የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ቢሮ ውስጥና የውጪ የወለል ምንጣፍ ሶፋና ወንበር እና በሥሩ ያሉት አዳራሾች ውስጥ ያሉትን በዘመናዊ ማሽን የእጥበት አገልግሎት ማጠብ የሚችሉ ድርጅቶች ማህበር በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳጠብ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ቢሮ ውስጥና የውጪ የወለል ምንጣፍ ሶፋና ወንበር እና በሥሩ ያሉት አዳራሾች ውስጥ ያሉትን በዘመናዊ ማሽን የእጥበት አገልግሎት ማጠብ የሚችሉ ድርጅቶች ማህበር በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳጠብ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡-
- በማጽዳትና እጥበት አገልግሎት ዘርፍ የተደራጁ ድርጅት ማህበራት፣
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ከግዥ ንብ/አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሽገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ሰነዶችን አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
