የአራዳ ክፍለ ከ/ወ/07/ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የንግድ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
- የታደሰ የ2017 ንግድ ፍቃድ ያለው
- ሌላ የንግድ ቤት የሌለው መሆኑን ካለበት ወረዳ አጽፎ መምጣት የሚችል
- Cpo ባለ 20 ሺህ ብር (ሀያ ሺህ ብር) ለአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል አድራሻ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አሰርቶ መምጣት የሚችል
- ለአንድ ካሬ መነሻ ዋጋ 1500 ብር /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር/ ነው።
- የንግድ ቤቱን ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል የማይመለስ 500 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላል።
- የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች ውድድር ላይ መሳተፍ አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ቅጽ ኦርጅናል መሆን አለበት።
- የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ የተሟላ ሰነድ ነው የሚባለው በትክክል ተሞልቶ እና ተፈርሞበት ዋናው /ኦርጃናሉ ሲቀርብ ብቻ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀረበውን የጨረታ ጠቅላላ ዋጋ በአሃዝና በፊደል ከዚህ ሰነድ ጋር በክፍል 3 ተያይዞ በሚገኘው የጨረታ ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ቅጽ/ ሞልቶ ማቅረብ አለበት።
- ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ስርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ቤቱን ጋዜጣ ላይ በወጣው አድራሻ መሰረት በአካል አይተው መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ከፍል 3 /ሶስት/ የተመለከተውን የንግድ ቤት የጨረታ ማቅረቢያ ዋጋ ሰነድ /ቅጽ/ ሞልቶ በፖስታ በማሸግ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ እና አስፈላጊ መረጃዎችን ማስገባት አለበት፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ በሚሆኑበት ጊዜ የሚጠበቅባቸውን ክፍያ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ በመክፈልና ለመከራየት በመዋዋል ንግድ ቤቱን ይረከባሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመከራየት ለአንድ ካሬ ሜትር የሚሰጡትን የሚከራዩበትን ዋጋ እና እንዲሁም ጠቅላላ ወርሃዊ የኪራይ ዋጋን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ቅጽ/ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቹ ለሚወዳደርበት የንግድ ቤት ሞልቶ ከሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ቅጽ/ የጨረታ ሰነዱን ሲገዛ የከፈለበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አብሮ አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የንግድ ቤቱ በጨረታ አሸንፎ የሚከራይ ግለሰብ በንግድ ቤቱ ውስጥ በንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አዋጅ የሚከለከሉ /የማይፈቀዱ የንግድ መስኮች መሰማራት አይችልም።
- በንግድ ቤቱ ላይ ከተራ ቁ.15 ከተመለከተው ውጪ የነዋሪውን ፀጥታ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የጋራ ኑሮን ለሚያውኩ ወይም ሕገወጥ ለሆኑ የንግድ እንቅስቃሴዎች አገልግሎት መዋሉ ሲታወቅና ለወረዳው ቅሬታ ሲቀርብ ወረዳው ተገቢውን አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይችላል።
- የጨረታው አሸናፊ በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቤቱ ለመከራየት ውል መፈፀም አለበት።
- በጨረታው አንደኛ የወጣው አሸናፊ በተራ ቁ.18 መሰረት ቀርቦ ለመከራየት ውል ካልፈፀመ ተጫራቹ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /cpo/ ተወርሶ ሁለተኛ የወጣው ተጫራች የወረዳው አስተዳደር በሚያስቀምጠው 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አንደኛ የወጣው አሸናፊ በሰጠው ዋጋ ሊከራይ ይችላሉ። ሁለተኛ የወጣው ተጫራች ፍቃደኛ ካልሆነ በተመሳሳይ ሁኔታ ሶስተኛ የወጣው ተጫራች ፍቃደኛ ከሆነ ኮሚቴው በማያስቀምጠው 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ አንደኛ የወጣው አሸናፊ በሰጠው ዋጋ ሊከራይ ይችላል።
- ተጫራቹ ማንነቱን የሚገልጽ የአዲስ አበባ አስተዳደር የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ ሰነዱን ሲመልስ አብሮ ማያያዝ ይኖርበታል።
- ይህ ጨረታ የሚቆየው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ8ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ መረጃ ከተፈለገ አራዳ ክፍለ ከ/ወ/07/ፋይናንስ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ማግኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0111222848 በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአራዳ ክፍለ ከ/ወ/07/ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
