የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ጀርባ ባልቻ ት/ት ቤት ፊት ለፊት ያስገነባውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ባለ አራት ወለል ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለካፌ፣ ለሱቅ ለአዳራሽ ኪራይ እና የተለያዩ አገልግሎቶች መስጠት የሚችል ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
Guraghe Development and Cultural Association (የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር)
የህንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ጀርባ ባልቻ ት/ት ቤት ፊት ለፊት ያስገነባውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ባለ አራት ወለል ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለካፌ፣ ለሱቅ ለአዳራሽ ኪራይ እና የተለያዩ አገልግሎቶች መስጠት የሚችል ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች ህንፃውን በአካል በመገኘት መመልከት የሚችሉ መሆኑን እየገልጽን
- በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድና የግብር መክፈያ ቁጥር ሰርቲፊኬት ኮፒ የቫት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ
- የዋጋ መወዳደሪያ ማቅረቢያ ቅጽ ፒያሳ አራዳ ህንፃ ፊት ለፊት የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ቢሮ ውስጥ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የራሳቸውን ቅፅ መጠቀም አይችሉም።
- ተጫራቾች የዋጋ መወዳሪያቸውን የሚያስገቡት በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ፒያሳ አራዳ ህንፃ ፊት ለፊት የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ቢሮ ውስጥ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461150125 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታው መክፈቻና መዝጊያ የሚሆነው ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሠዓት ተዘግቶ 10:30 ይከፈታል።
