Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውል በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ሀላባ ቁሊቶ ከተማ ፋይናንስ 03/2017

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውል በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ (እስቴሽነሪ)                                ሎት 5 መስተንግዶ (ረፍረሽመንት)

ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች                        ሎት 6 ህትመት

ሎት 3 ፈርኒቸር                                         ሎት 7 የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች

ሎት 4 ሞተር ሳይክል                                   ሎት 8 የደንብ ልብስ

  • ህጋዊ የሆነ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  • የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  • በዚህም መሰረት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ የስራ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
  • ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመወዳደሪያ የቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ እንዲሁም የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናል የያዘ አንድ ኮፒ በእናት ኤንቨሎፕ በማድረግ በሰም በማሸግ እናት ላይ ህጋዊ ማህተም ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  • እያንዳንዱ ተጫራች ሙሉ አድራሻውን በግልጽ በሚታይ ሁኔታ በኢንቨሎፕ አናት ላይ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ 5,000 (አምስት ሺ ብር) የኢትዮጵያ ብር ሲፒኦ ማሲያዝ ይኖርበታል።
  • ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት በ16ኛው ቀን ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል እለቱ የእረፍት ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር-0465560063/0465560853 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠይቅ ይችላሉ፡፡
  • ድረ ገጽ www.kulitofinance.org ማግኘት ይችላሉ፡፡

አሰሪው መስሪያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender