በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ሰራተኞችን የስራ አልባሳት (ዩኒፎርም) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢኤአ‐ባሪ/ግብጨ/007/2017
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ሰራተኞችን የስራ አልባሳት (ዩኒፎርም) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ሳይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፤
- የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ዋና መ/ቤት ባሕር ዳር ቀበሌ 05 ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦሪጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-3-20-51-12 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን
