የመንግሥት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን እንጅባራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሃምሌ 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 አመት መከራየት ይፈልጋል።
የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር እንጅባራ
የቤት ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የመንግሥት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን እንጅባራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሃምሌ 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 አመት መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም ፡-
- በስማቸው የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸው
- የዘመኑ የአፈር ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ያላቸው
- ለቢሮ አገልግሎት የሚፈለገው ቤት ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን ህንፃው ግራውንድ /G+0/ ያለው ሆኖ ከ18 ክፍሎች በላይ ያሉትና 2ቱ ክፍሎች ስፋት እያንዳንዳቸው ከ16ካሬ ያላነሱ፤ 5ቱ ከፍሎች እያንዳንዳቸው ከ9ካሬ ያላነሱ፤ 5ቱ ከፍሎች እያንዳንዳቸው ከ20 ካሬ ያላነሱ፤1ዱ ከፍል ከ25ካሬ ያላነሰ፤ 2ክፍሎች እያንዳንዳቸው 35ካሬ ያላነሱ እና 3ክፍሎች ከ12 ካሬ ያላነሱ መሆን አለባቸው።
- ለተገልጋይ ምቹ የሆነና በአካባቢው የተዘረጋ የስልክ መስመር ያለው
- የቧንቧ ውሃ፣ መብራት የራሱ ቆጣሪና የተሟላ ሶኬት ያለው፣ንፁህ መፀዳጃ ቤት ያለው
- የጥበቃ ቤት ያለው ከሌለው ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ
- የራሱ ግቢና አጥር ያለው
- የቤቱ ስፋት ከ24 ሰራተኞች በላይ ሊይዝ የሚችል።
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር1-8 የተጠቀሱትን የሚያሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እንጅባራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ድረስ በመቅረብ መጫረቻ ሰነዱን በመወሰድ የሚከራዩትበትን ዋጋ በመሙላት ከይዞታ ማረጋገጫ እና የአፈር ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ጋር በደንብ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የምንከራየው ቤት ለተገልጋይ አመቺ መሆኑ በኮሚቴ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ሰዓት በጽ/ቤቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አያግደውም፡፡ የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተደነገገ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር-058 227 1027/1039
የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን አንጅበሪ ቅ/ጽ/ቤት ቀበሌ 05 ጤና ጣቢያው አካባቢ
የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
እንጅባራ
