በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የጽዳት አገልግሎት በሶስተኛ ወገን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ለ3ኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የጽዳት አገልግሎት በሶስተኛ ወገን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ መንግስታዊ ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቲ.ኦ.ቲ/ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ሆኖ እነኝህን ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ፡-
-
ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013485236 በማስገባት 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብር 10,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
-
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀን አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
-
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም የታሸገ ፖስታ በማድረግ 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
-
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል።
-
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 046-220-42-24/046-212-34-68 ይጠቀሙ።
አድራሻ፦ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ።
በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
