የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ እና የኤሌክትሪክ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ እና የኤሌክትሪክ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችል፤
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋርአያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)፣ በጥሬ ገንዘብ እና የባንክ ዋስትና (በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ 1 ኦሪጅናል እንዲሁም 1 ኮፒ በአጠቃላይ 2 ፖስታዎችን ማለትም ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስገቡ እየገለጽን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ነገር ግን 21ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ሲገለጽለት የውል ማስከበሪያ 10% ብር በሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የባንክ ዋስትና (በሁኔታዎች ላይያልተመሰረተ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033-311-77-52 0920208146: 0914613590: 0989887862 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደሴ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
