የአማራ ደን ኢንተርኘራይዝ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ለ 2017 ዓ/ም ለሰራተኞች የሚውል 6000 ቲትረን ብትን ጨርቅ ሸሚዝ፣ ካቦርት ኮፍያ ፣ የዝናብ ልብስ ፣ ጫማ ፣ የቲዎታ መኪና ብሪጅ ስቶን ጎማ ከነካለማደሪያው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የደንብ ልብስና የመኪና ጎማ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ
የአማራ ደን ኢንተርኘራይዝ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ለ 2017 ዓ/ም ለሰራተኞች የሚውል 6000 ቲትረን ብትን ጨርቅ ሸሚዝ፣ ካቦርት ኮፍያ ፣ የዝናብ ልብስ ፣ ጫማ ፣ የቲዎታ መኪና ብሪጅ ስቶን ጎማ ከነካለማደሪያው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ቲን ነምበር ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና መረጃ ኦርጅናል የማይመለስ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው መቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የንግድ ፍቃድ ያለው መሆን አለባቸው ::
- ተጫራቾች የምታቀርቡበት ዋጋ ከ 200000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ/ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 3 በመሄድ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የመጨረሻ ሰነዶቻቸው ላይ ስም እና አድራሻ በመጻፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በመጨመር በቀን 24/06/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ። ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች ቢኖሩም ባይኖሩም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ እና ከ 10000 ብር በታች ከሆነ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን እቃ /ናሙና/ የየራሳችሁን : ናሙና በጨረታው እለት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የራሱን ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል ። በጨረታው እለት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የራሱን ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የሚጫረትበትን አልባሳት እና የመኪና ጎማ በሰነዱ መሰረት አልባሳት ፤ጫማና ጎማ ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል በፖስታው ላይ የተወዳደረበት አልባሳት አይነት ከላይ መጻፍ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት / ግለሰብ አሸናፊነቱ ሲታወቅ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ በመያዝ ውል በመውሰድ ወደ ስራ መግባት ይኖርበታል፡፡
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር አለበት ስርዝ ድልዝ ካለ በፊርማ መረጋገጥ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0913126384 /0945149854/
Tel 0335511094/0335510185 Fax 0335511094 po/Box 150 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ
