የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት መብራት ሃይል አካባቢ ጉሙሩክ ፊት ለፊት ያስገነባውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ባለ አራት ወለል ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለካፌ፣ ለሱቅ እና የተለያዩ አገለግሎቶች መስጠት የሚችል ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Conformity Assessment Enterprise -ECAE (የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት)
የህንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት መብራት ሃይል አካባቢ ጉሙሩክ ፊት ለፊት ያስገነባውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ባለ አራት ወለል ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለካፌ፣ ለሱቅ እና የተለያዩ አገለግሎቶች መስጠት የሚችል ህንጻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ጨረታው በአዲስ ዘመን እና በሪፖርተር ጋዜጦች ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች የሚከራዩ ክፍሎችን ዓይነትና ስፋት በአዳማ ከተማ መብራት ሃይል አካባቢ ከሚገኘው የኢተምድ ማዕከላዊ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አዳማ በአካል በመገኘት መመልከት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድና የግብር መክፈያ ቁጥር ሰርተፊኬት ኮፒ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የኪራዩ የመነሻ ዋጋ በካሬ ለምድር ቤት 1500 ብር ፤ ለ1ኛ ፎቅ 1000 ብር፣ ለ2ኛ ፎቅ 800 ብር ለ4ኛ ፎቅ 400 ነው።
- የዋጋ መወዳደሪያ ማቅረቢያ ቅጽ የሚወዳደሩበትን ክፍሎች ከለዩና ከወሰኑ ማዕከላዊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አዳማ ወይም አዲስ አበባ መገናኛ አምቼ አጠገብ የጥራት መንደር ግቢ ውስጥ ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤ ተጫራቾች የራሳቸውን ቅፅ መጠቀም አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ መወዳሪያቸውን የሚያስገቡት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አዳማ በሚገኘው ማዕከላዊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ መገናኛ አምቼ አጠገብ የጥራት መንደር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 20 93 79 39፤ 09 11 20 48 47 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታው መክፈቻና መዝጊያ የሚሆነው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀን ይሆናል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት
