ንስር ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ በሰንጋ ተራ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች አካባቢ የሚገኙ እና በስሙ የተመዘገቡ ሁለት የንግድ ቤቶች (ሱቆች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Nisir Microfinance (ንስር ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ)
የንግድ ቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ንስር ማይክሮፋይናንስ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ በሰንጋ ተራ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች አካባቢ የሚገኙ እና በስሙ የተመዘገቡ ሁለት የንግድ ቤቶች (ሱቆች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት የንግድ ቤቶቹን (ሱቆቹን) ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በመገንዘብ ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የንግድ ቤቶቹ አድራሻ |
የቤት ቂጥር |
የንግድ ቤቶቹ ስፋት በሜ2 |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
ልደታ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 09፤ ሰንጋ ተራ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች፤ ሕንፃ ቁ.02 ፤ 2ኛ ፎቅ |
ል.9/78/13822/100 |
92.81 ሜ2 |
ብር 14,600,000.00 |
|
2 |
ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09፤ ሰንጋ ተራ የጋራ መኖሪያና ንግድ ቤቶች ሕንፃ ቁ.03 2ኛ ፎቅ |
ል.9/78/13820/100 |
93.98 ሜ2 |
ብር 13,800,000.00 |
መስፈርቶች ፡-
-
- ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከየካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 1,000.oo (አንድ ሺህ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ለሚጫረቱት ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በንስር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ በመክፈልና ውል በመፈፀም በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለተቋሙ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በጨረታው ላላሽነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና እና ግብር ካለ ገዥው (አሸናፊው) ይከፍላል።
- የንግድ ቤቶቹን ለማየት የሚፈልግ ተጫራች ከየካቲት 03 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) ከተቋሙ ጋር በመነጋገርፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይችላል።
- ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።
- ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0115 62 23 71/0115 62 23 25 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ንስር ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ
