በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አላቂ የጽዳት እቃዎች እና የትራንስፖርት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- 003/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አላቂ የጽዳት እቃዎች እና የትራንስፖርት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው::
-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ቦ/ከ/ወ/11/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው፡፡
ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-
- ህጋዊ መንጃ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሲፒኦ 2,000 ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ያላቸው፤
- ሶስተኛ ወገን /ኢንሹራንስ⁄ ያላቸው፤
- ቦሎ ያላቸው እና የታደሰ የሆነ፤
- በዘርፉ የተሰማሩ
ሎት ቁጥር ሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ. ብር
ሎት 1. አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣
ሎት 2. የትራንስፖርት አገልገሎት፣ 2,500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/፣
-
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመስስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 11 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ወረዳ 11 ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 004 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ሰሚት ኮንዶሚንየም ሶስተኛ በር አደባባዩን ወረድ ብሎ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወ/11/ፋ/ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር :- 011-8-93-15-22
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት
