የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት የጽዳት የአውትሶርስ የአገልግሎት ግዥ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል ፡፡
Debre Markos University (ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ማ/ዩብ/ግ/ጨ/04/2017
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት የጽዳት የአውትሶርስ የአገልግሎት ግዥ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከዚህ በታች ማለትም፡-
- በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- አሸናፊው ድርጅት ለሁለት ዓመት ውል በመያዝ ለጤና ካምፓስ የፅዳት አገልግሎት ይሰጣል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሎት 1 ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል። ወይም በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት ከላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን የሚገልጽ የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ከሚገኘው ቢሮአችን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር / በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዩኒቨርሲቲው ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000017980517 ደረሰኝ በማቅርብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ፋይናሽያል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ሰነዶችን ኮፒ ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ከ8ኛ ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ8 የስራ ቀናት ውስጥ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 15 ቀናት በኋላ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻት በተገኙበት 4:30 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል።
- የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 771 66 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
