የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ አላቂ ዕቃዎች፤ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎችና ኤሌክትሮኒክሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ
- አላቂ ዕቃዎች፤ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎችና ኤሌክትሮኒክሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከህጋዊ ባንክ CPO ወይም በካሽ ለ10,000 ከሚያቀርቡት ከዕቃ ጋር በተናጥል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈር የድርጅቱን ማህተም መምታት ያለባቸው ሲሆን በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎች በአንድ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የደ/ኢት/ክ/መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ላይ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል።
- ይህ ጨረታ ከፍት ሆኖ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ የደ/ኢት/ከ/መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና አሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
- ይህ የጨረታ ዋጋ ለ45 የሥራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የደ/ ኢት/ክ/መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 180 2396 /046 180 4910 የደ/ኢት/ክ/መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ
