የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት "Confort plastic doctor shoes" ለአንደኛ ጊዜ እና የጽዳት እቃዎች ለሶስተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት ፡-
- "Confort plastic doctor shoes" ለአንደኛ ጊዜ
- የጽዳት እቃዎች ለሶስተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላለችሁ፡፡
- 2016/17 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያልችሁ እንዲሁም የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈለ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየ ብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ሰርዝ ድልዝ ያለው፣ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ 100 /መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው፡፡
- "Confort plastic doctor shoes" ጨረታው የሚከፈተው በ07/05/2017 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጽዳት እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ07/05/2017 ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ፡-
- "Confort plastic doctor shoes" 6000 /ስድስት ሺ/ ብር
- ለጽዳት እቃዎች 8000 /ስምንት ሺ/ ብር በ"CBE, CBO, እና በSingq" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0228123956 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
