በአ/አ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከ/ወ6 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት እቃ ግዥ ለ2017 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጉለሌ ክ/ከተማ ወ6/ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 003/2017 ዓ.ም
በአ/አ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከ/ወ6 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት እቃ ግዥ ለ2017 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታው አይነት
ሎት 1. የአላቂ የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 15000 ብር
ሎት 2. የቢሮ የፅህፈት መሳሪያ ጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን ብር 10000
ሎት 3. የደንብ ልብስ ጨርቅ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን ብር 5000
ሎት 4. የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1500
በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች
1ኛ. በጨረታ የሚወደዳሩ ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በስማቸው ያላቸውን የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የግብር ግዴታቸውን በግብር አስገቢ በባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ
2ኛ. ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TINnumbr/VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
3ኛ. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላሉ።
4ኛ. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ስም ማህተም ስልከ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት ፡፡ የሚጫረቱበትን የዕቃ አይነት በመጥቀስ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት በስራ ሰአት በቢሮ ቁጥር 14 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5ኛ. ማንኛውም ተጫራች የመንግስት ግዥ አቅራቢነት የተመዘገበ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
6ኛ. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህራዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ባበቃ በመጨረሻ ቀን 10፡30 ሰዓት ይታሸግና በማግስቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
7ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡ እና የጨረታውን አሸናፊ 10% የጨረታው ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8ኛ. አሸናፊው ተጫራች ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 10፡00 ንብረቶችን በራሱ በማጓጓዝ ማስጫኛና ማውረጃውን ጨምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አሰተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ማውረድ ይኖርበታል።
9ኛ. ጽ/ቤቱ የሚያጫርተውን የዕቃ ብዛት 20 ፐርሰንት መቀነስና መጨመር ይችላል፡፡
10ኛ. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጫራቾች ማብራራያ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0111-22-67-04 እና 0118-12-24-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
11ኛ. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ማቅረብ የማይችል ከሆነ ገላጭ እስፔስፍኬሽን ማምጣት አልያም እቃውን የሚያሳይ ጥርት ያለፎቶ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ ፡- ሽሮሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፊያ 500 ሜትር ገባ ብሎ።
በአ/አ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክ/ከ/ወ6 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
