የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የእቃና የአገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2017
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችም፡-
1. ሶዴም ሃይፖ ክሎራይት 10%
2. የኤሌክትሪክ እቃዎች
3. ቧንቧ መገጣጠሚያ
4. የጽህፈት መሳሪያ
5. ብትን ጨርቅ
6. የተሰፉ ልብሶች
7. ልብስ ስፌት
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዝገባቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ለጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በባንከ የተረጋገጠ 1 ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፤
- ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ከ/ ውሃ /አገ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም።
- በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ መ/ቤቱ አይሸፍንም ።
- ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ /መንገድ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ደ/ማ/ ከ/ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587716840: 0587711058: 0587711520
ማሳሰቢያ ፡-
- ኬሚካሉ በየወሩ ተከፋፍሎ በዓመቱ ውስጥ የሚመጣ መሆኑ ይታወቅ
- የቧንቧና መገጣጠሚያ እቃዎች፤ ብትን ጨርቅ እና ሸሚዝ ጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት የእቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን የእቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የእቃን አይነት እንጂ እቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መጥታችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን።
- ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
- የደንብ ልብስ ስፌቱ የሚከናወነው ጽ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሆኖ ክፍያ የሚፈፀመው በሰፋው ልብስ ልክ ነው።
በደ/ማ/ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የገቢ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት
