Tender Detail

Tender Details

  • Company Bahir Dar University (ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ)
  • Address ባህር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0583202052
  • Websitehttps://www.bdu.edu.et/
  • Deadline20 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት ሃአግ/ባዳዩማግዥ/5/2017 የደንብ ልብስ እና የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ግዥ መግዛት ይፈልጋል።

Bahir Dar University (ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ)


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት ዓመት ሃአግ/ባዳዩማግዥ/5/2017 የደንብ ልብስ እና የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ግዥ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ- ገጽ(eGP) የተመዘገበ፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅፅ ላይ ማህተምና ፊርማ የተደረገበት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉና የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆነው ሁሉንም ሠነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ በማድረግ እና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በአግባቡ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስም 1000013099522 በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ ከዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ ክፍል የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ሕንፃ ማዕከላዊ ግዥ ክፍል G+2 ቢሮ ቁ-201 መግዛት ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለደንብ ልብስ እና የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች ግዥ፡- የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፣ በባንክ በተረጋገጠ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ለሚፈልጉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስም 1000013099522 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ ከዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ ክፍል የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
  5. በአነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ከአደራጃቸው ተቋም በጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ዋናውን ደብዳቤ የሚወዳደሩበትን ሎት እና የብር መጠን በመጥቀስ ያለ ክፍያ በነፃ የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማግኘት ይችላሉ።
  6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነቱ ታውቆ ውሉ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  7. ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ሕንፃ ማዕከላዊ ግዥ ክፍል G+2 ቢሮ ቁ-201 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. የደንብ ልብስ እና የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች ግዥ - ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይሆናል።
  10. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

         ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0583202052 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡

 

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Save Tender