Tender Detail

Tender Details

  • Company Ambo University (አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል)
  • Address አምቦ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-60-99-79
  • Website
  • Deadline18 Nov 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Catering And Cafeteria Services

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፈራል ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ተኝተው ለሚታከሙት ህሙማን ለአንድ ዓመት በራሳቸው ሙሉ ወጪውን ሸፍነው በሆስፒታሉ ግቢ ወይም አቅራቢያ ምግብ አዘጋጅተው ከሚያቀርቡት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Ambo University (አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል)


በድጋሚ  የወጣ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር ፡- አዩ/ግ/አስ/03/2017 ዓ.ም

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፈራል ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ተኝተው ለሚታከሙት ህሙማን ለአንድ ዓመት በራሳቸው ሙሉ ወጪውን ሸፍነው በሆስፒታሉ ግቢ ወይም አቅራቢያ ምግብ አዘጋጅተው ከሚያቀርቡት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሠረት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ እና የTIN የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. በተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት በአንድ ላይ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. የጨረታ ሰነዱን የማይመሰስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዩኒቨርሲቲው ሪፈራል ሆስፒታል ግዥ የሥራ ከፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ለተሸናፊዎች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10.000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ አሰርተው ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቹ ማብሰያ ዕቃዎችንም ሆነ የሚያዘጋጅበትን ቤት /ኪችን/ ሆስፒታሉ በሚሰጠው ቦታ ላይ ያዘጋጃል፡፡
  6. ተጫራቾች ሪፈራል ሆስፒታሉ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ምግብ ጠቅላላ ሳይቀር የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ዋጋ የሚሞሉበትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ ⁄ ኤንቨሎፕ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
  9. ጨረታው ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ3፡45 ሰዓት ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሪፈራል ሆስፒታሉ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  10. የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስቀርም፡፡
  11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈጋቸው በስልክ ቁጥር፡- 011-2-60-99-79 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. ሪፈራል ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አምቦ  ዩኒቨርሲቲ  ሪፈራል  ሆስፒታል

Save Tender