Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ካስገነባቸው ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ/ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በውጪ ምንዛሪ ተመን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ አገ/11/03/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


የ5ኛ  ዙር  የመኖሪያ / ገስት  ሀውስ

ቤቶች  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  መለያ  ቁጥር  ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/03/2017

  1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ካስገነባቸው ዘመናዊ ህንፃዎች ውስጥ ለመኖሪያ/ገስት ሃውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በውጪ ምንዛሪ ተመን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ አገ/11/03/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
  2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የመኖሪያ/ገስት ሃውስ ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው::
  3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልከቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሠረት ነው::
  4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን ለገሐር በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢያ አዳራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ወይም ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሀያ አምስት ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ከፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 011-8-55-36-12 ወይም 011-8-55-36-17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ዌብሳይት / website www.fhc.gov.et

የፖ.ሣ.ቁ.P.O. Box 299

ፋክስ ቁጥር: 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46

 

የፌዴራል  ቤቶች  ኮርፖሬሽን

Save Tender