Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Address አዲስ አበባ ሬስቶራንት ወረድ ብሎ የአራዳ ከ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1 26 62 73
  • Website
  • Deadline18 Nov 2024, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Textile, Garment & Leather

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት 2017 ዓ.ም የበጀት አመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ከነስፌቱ፣ ለ ቋሚ እቃዎች የስፖርት ትጥቅ ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ የህትመት ስራዎች ፣ ልዩ መሳሪያዎችን፣  የፕላንት ማሽነሪ ጥገናና ሰርቪስ ፣ የህንፃ ጥገናና የፓርቲሽን ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል ::

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


  የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 1

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት 2017 ዓ.ም የበጀት አመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ከነስፌቱ፣ ለ ቋሚ እቃዎች የስፖርት ትጥቅ ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ የህትመት ስራዎች ፣ ልዩ መሳሪያዎችን፣  የፕላንት ማሽነሪ ጥገናና ሰርቪስ ፣ የህንፃ ጥገናና የፓርቲሽን ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል :: በዚህ መሰረት በጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ሁኔታ ማሟለትና ማቅረብ አለባቸው ::

  1. በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ተጫራቶች በተሰማሩበት የንግድ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለውና ዋናውን በማሳየት ኮፒውን ማያያዝ አለበት ፡፡
  3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፍኬት) ያለውና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ባሸነፏቸው ኤሌከትሮኒክስ እቃዎች የሁለት አመት ዋስትና እና የተለያዩ የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ የማባዣ ቀለሞች /ቶነሮች/ የአንድ አመት ዋስትና መስጠት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ አይነት ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ያቀረቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ፐርሰንት ያልበጠ /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው::
  9. በሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ VAT 15% ተሰልቶ መካተት ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን VAT እንደተካተተበት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  10. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦረጅናል ላይ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ላይ ማህተም በማድረግ ከኮፒ ጋር በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ስአት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ይከፈታል ፡፡ ነገር ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. መ/ቤቱ የሚጫረተውን እቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
  14. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የጉልበት ወጪ በተቋሙ ቅጥር ጊቢ በሚገኘው ንብረት ክፍል ማድረስ አለባቸው::
  15. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡- 011 1 26 62 73/ 011 1 58 57 06/

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ሬስቶራንት ወረድ ብሎ የአራዳ ከ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05

የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ ት/ቤት

Save Tender