በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴል አስተዳደር በግቢው ውስጥ የሚገኘውን የመናፈሻው ስፍራ በስተግራ በኩል የሚገኘው ሲሆን በዚህም ባለን ክፍት ቦታ ላይ ድርጅቱ አገልግሎቱን ሙሉ ለማድረግ በማሰብ የስጋ ቤት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው ድርጅቶች ቦታውን ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል
ጨረታ ማስታወቂያ
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴል አስተዳደር በግቢው ውስጥ የሚገኘውን የመናፈሻው ስፍራ በስተግራ በኩል የሚገኘው ሲሆን በዚህም ባለን ክፍት ቦታ ላይ ድርጅቱ አገልግሎቱን ሙሉ ለማድረግ በማሰብ የስጋ ቤት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው ድርጅቶች ቦታውን ለማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በድርጅቱ ህግና ደንብ መሠረት እና በጨረታ ሰነዱ መስፈርት ከዚህ በታች በቀረበው ቅድመ ሁኔታ የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአካል በመቅረብ እና በማይመለስ 300 ብር በመክፈል መግዛትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለመወዳደር የሚያስችሉ መስፈርቶች ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1. በዘርፉ የ2016 ዓ.ም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
3. ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነ/ች፡፡
4. የታክስ ክሊራንስ (በጨረታ የመሳተፍ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል)
5. የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው የሚዘጋው በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሲሆን ሳጥኑ ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ሰዓት በሆቴሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ህጋዊ ተወዳዳሪ ወይም ተወካይ እና የጨረታ ኮሚቴው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 5,000.00/አምስት ሺህ ብር/ በገነት ሆቴል ስም ሲፒኦ አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ - አዲስ አበባ ሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ /ገነት ሆቴል/
ለበለጠ መረጃ፡-
ስልክ ቁጥር፡- 0911250641 -0115 51 47 70
አድራሻ፡ ሞዛምቢክ ጎዳና፤ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ሳይ
Address: Mozambique Street, on the way from Mexico to Kera
ስ.ቁ Telephone): +251-115-51-47-70/+251-115-50-47-01
የመ.ሳ.ቁ (P.o. Box): 397
በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴል
