Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 Apr 2023, 4:29 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2015 ዓ.ም የተለያዩ የደንብ ልብሶች ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ የፅዳት ዕቃዎች ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


ለ2ኛ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2015

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2015 ዓ.ም

  • የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣
  • የፅህፈት መሳሪያዎች ፣
  • የፅዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፤

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

  1. በመንግስት ግዢ በዕቃ አቅራቢነት ውስጥ የተመዘገቡ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ከሰጠነው የጨረታ ሰነድ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት ይኖረውም።
  3. ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ሠነድ ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው ።
  4. ለደንብ ልብስ ግዥ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ለጽዳት ዕቃዎችና ለፅህፈት መሳሪያዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  6. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የውሉን 10%ማስያዝ ይኖርበታል።
  7. ገዢው መስሪያ ቤት በጨረታው ወቅት ከግዢው መጠን 25% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል በተጨማሪም፤
  8. ገዢው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ ከውሉ መጠን 20% ብዛት እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጨምር ይችላል።
  9. ተጫራቾች በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ናሙናቸውን ከጨረታ መክፈቻው በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ እንዲሁም ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ ) በመhፈል በቂ/ክ/ከ/ የወረዳ 07 ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  14. ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡትን ዋጋ የሚቆይበትን ጊዜ ቢያንስ ለ 60 ቀን መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  15. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
  16. የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ : በስልክ ቁጥር 011 515 8838 አድራሻ፡

ብሄራዊ ከበድሉ ህንጻ በስተጀርባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ

በአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት አዲስ አበባ

Save Tender