የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር Addis Ababa Prosperity Party Office-01/2015
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
-
- ሎት፡ 1 የጽሕፈት መሣሪያ ዕቃዎች
- ሎት፡ 2 የፅዳት መሣሪያ ዕቃዎች
- ሎት፡ 3 የመኪና ዲኮር ዕቃዎች
- ሎት፡ 4 ቋሚ ዕቃዎች
- ሎት፡ 5 የተዘጋጁ ደንብ ልብሶችና ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1.1 የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣
1.2 የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፣
1.3 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ፣
1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ያላቸው፣
1.5 በግዢ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ሊስት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
1.6 ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚገልጽ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ጎላጎል ታወር ፊት ለፊት ሃያ ሁለት ትራፊከ ፖሊስ ሕንፃ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ስድስተኛ ፎቅ ሂሳብ ክፍል በግንባር በመቅረብ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ መግዛት ይቻላል።
3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት 5000.00 (አምስት ሺ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ብቻ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ከሲ.ፒ.ኦ ውጪ የሚቀርብ ማስያዣ ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል። ተጫራቾች አሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
4 ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ ያልጠበቀ ዕቃ ማቅረብ ከአቅራቢነት ያሰርዛል።
5. ስርዝ ድርዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ወጪ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ብቻ የአንዳንዱ ዋጋ በጠቅላላ የዋጋ እና ቫትን አካቶ ያለውን ድምር በመጨመር ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት እና ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሽግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ ከ3 ቀናት በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
8. ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል። የጨረታው መከፈቻ ቀን የሥራ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
10. የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከውድድር ወጪ ይሆናል።
11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 667 4387 | 011 667 4430 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
