ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት Flat Stitching Wire & Rag (ቁርጥራጭ ጨርቅ) እና የዱቄት ሳሙና በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታ አንድ /ሎት1/፡- Flat Stitching Wire No. 21 ብዛት 400 ጥቅል ግዥ
- በጨረታ ሁለት/ሎት2/፡- Rag /ቁርጥራጭ ጨርቅ/ ብዛት 3,000 ኪሎ ግራም እና የዱቄት ሳሙና ባለ 200 ግራም ብዛት 3,000 ፓኬት ግዥ
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ አዲስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የእለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 200 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሽያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባር ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው በ26/8/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ /ከላይ የተገለጹ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፡ የጨረታ ማስከበሪያ/ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሰነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር 011-155-5230
ድረ ገጽ (www.ethbspe.org )
Berhanena Selam Printing Enterprise
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
