Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Sep 2022, 12:06 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በምስራቅ ሸዋ ዞን የጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የደንብ ልብሶች ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና አላቂና ቋሚ ፣ የቢሮ ዕቃዎች የጽዳት ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የመኪና ዕቃዎችና ጎማዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ ፈርኒቸሮች ፣ የተለያዩ ለቴክኒክና ሙያ የት/ቤት ስልጠና ተቋም መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ሸዋ ዞን የጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚገለግሉ

  • የደንብ ልብሶች ፣
  • የጽህፈት መሳሪያዎችና አላቂና ቋሚ ፣
  • የቢሮ ዕቃዎች ፣ 
  • የጽዳት ዕቃዎች ፣
  • የተለያዩ የመኪና ዕቃዎችና ጎማዎች ፣
  • ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣  
  • ፈርኒቸሮች ፣
  • የተለያዩ ለቴክኒክና ሙያ የት/ቤት ስልጠና ተቋም መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2 ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው ሆኖ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብ የአቅራቢዎች መዝገብ ዌብሳይት ላይ ተመዝግበው ያሉ እና በአሁኑ ወቅት ዌብሳይት ላይ መገኘታቸውን የሚያመላክት ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ

  • ሎት 1. የደንብ ልብሶች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ብቻ
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂና ቋሚ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ
  • ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች ግዢ ጨረታ ማስከበሪያ 2500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ
  • ሎት 4. የተለያዩ መኪና ዕቃዎች እና ጎማዎች ግዢ ጨረታ ማስከበሪያ 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ብቻ
  • ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዢ ጨረታ ማስከበሪያ 8,000 (ስምንት ሺህ ብር) ብቻ
  •  ሎት 6. ፈርኒቸር እና ቢሮ እቃዎች ግዢ ጨረታ ማስከበሪያ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ብቻ
  • ሎት 7. የተለያዩ ለቴክኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና ተቋም መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች ግዢ ጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ

 የጨረታ ማስከበሪያ ብር በማስያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን እንዲሁም በጥቃቅንና አነሰተኛ የተደረጁ ማህበራት በእያንዳንዱ ሎት ከሚመለከተው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው የተሸናፊነታቸው እንዲረጋገጥ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት cpo ወዲውያኑ ይመለስላቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በግንቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6.ተጫራቾች ጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15)ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ይሸጥና ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሰነዱ መሸጥ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው 16ኛው የሥራ ቀን እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ማለትም /በአስራ ስድስተኛው /16ኛው/ የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም በጨረታው ለመካፈል የፈለጉ ማንኛውም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8. አሸናፈው ድርጅት ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርበታል።

9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፤-ጉምቢቹ ወረዳ ጨፌ ዶንሳ ከተማ ከአዲስ አበባ በሰንዳፋ በኩል 65 ኪ.ሜ. ሲሆን በደብረ ዘይት 8 ኪ.ሜ.

ስልክ ቁጥር 022-451-00-08 ወይም 0912230467 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ

የጌምቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender