በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የጽሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ ፈርኒቸር (የቢሮ) ዕቃዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞች የደንብ ልብሶች ፣ የመንግስት ሰራተኞች የደንብ ጫማዎች ፣ የመኪና ጎማዎች ፣ የሞተር ጎማዎችን ፣ ሞተር ሳይክሎችን ሕጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 1/ 2015
በቡኖ በደሌ ዞን የሚገኝ የዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙት መ/መ/ቤቶች (ዲዴሳ ሆስፒታልንና የዲዴሳ ወረዳ ቴ/ሙያ/ትምና/ሥልጠና ኮሌጅን ጨምሮ) የሚያስፈልጉትን ዕቃዎች፡-
እነሱም፦
- የጽሕፈት መሣሪያዎችና
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፣
- ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ፈርኒቸር (የቢሮ) ዕቃዎች፣
- የመንግስት ሰራተኞች የደንብ ልብሶች፣
- የመንግስት ሰራተኞች የደንብ ጫማዎች፣
- የመኪና ጎማዎች፣
- የሞተር ጎማዎችን፣
- ሞተር ሳይክሎችን ሕጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁና ማቅረብ የምትችሉ።
- የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ።
- ተወሪዳዳዎች በሀገር ውስጥ ጨረታ ለመወዳዳር የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሀገር ወስጥ ገቢ መ/ቤት ወይም ከጉሙሩh ባለስልጣን ከሀገ ውስጥ ገቢ ወይም ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
- በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ የዕቃው ሞዴል የተመረተበት ዓ/ም የተመረተበት ሀገር ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ ማቅረብ አለባቸው። ተወዳዳሪዎች በሁሉም የዕቃ ዓይነቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የህጋዊ ሠነዶቹን ማስረጃዎች ማለትም ከላይ ከተራ ቁጥር 1_4 የተጠቀሱትን ሠነዶች በኦሪጅናልና በኮፒ ለየብቻ በማድረግ የዋጋ ማቅረቢያና ህጋዊ ሠነዶቹን በሁለት ሁለት ኮፒ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ /ኤንቨሎፕ/ በማድረግ የሚመለከተውን የድርጅቱን ኃላፊ በማስፈረም ማህተም አድርገውበት በአጠቃላይ በአራት ፖስታ አድርገው በአንድ ላይ ማቅረብ አለባቸው የጨረታው ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- በ2014 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ተወዳድረው አሸንፈው ዕቃ ያላቀረቡትን ድርጅቶች የማናስተናግድ መሆኑንና፣ ማይክሮዎች ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ካላስያዙ በሚቀርበው ደብዳቤ ብቻ የማንቀበል መሆኑ ይታወቅ።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኦ ከላይ በተራ ቁጥር 6 ላይ ከተጠቀሰው ሠነድ ጋር ለብቻ በፖስታ በማሸግ ከህጋዊ የጨረታው ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈጻጻም የጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ግዥውን የሚያከናውን መ/ቤት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የተፈራረመውን ውል ሳይለውጥ ለመግዛት ትዕዛዝ ከተሰጠው ዕቃ ውስጥ 20% ጨምሮ የመግዛት ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ቤት ከቢሮ ቁጥር 4 በብር 100 የማይመለስ በመክፈል መግዛት ይችላሉ። ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 2/13/2014 6፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ2/13/2014 በ8፡30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል ቀኑ የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሰርዓት ላይ ባይገኙም የጨረታው ሂደት አይስተጓጉልም።
- የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ የማጓጓዣ የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ የሻጭ ግዴታ ይሆናል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-14 በተጠቀሱት ላይ የማይስማማ ድርጅት መሳተፍ አይችልም።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 443 0021፣ 0913 78 43 84፣ 0912 70 11 05
የዲዴሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
