Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Aug 2022, 11:21 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የገላን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 የበጀት ዓመት የጽሕፈት መሳሪያ ፣ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ፈርኒቸር ፣ ለቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ የሚያገለግሉ ዕቃዎች


የጨረታ ማስታወቂያ

በፊንፊኔ ዙሪያ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የገላን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 የበጀት ዓመት

  • የጽሕፈት መሳሪያ ፣
  • የጽዳት ዕቃዎች ፣
  • ፈርኒቸር ፣
  • ለቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ የሚያገለግሉ ዕቃዎች ፣
  • ደንብ ልብስ እና
  • ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መረጃዎች በማቅረብ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ
  3. የዕቃዎቹ ዝርዝር ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት(15) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 250.00 ( ሁለት መቶ ሃምሣ) ብር ገላን ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት በመhፈል ሰነዱን ከገላን ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ ስድስት ( 16) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በገላን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
  5. . ጨረታው በአስራ ስድስተኛው (16) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ  ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በገላን ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል:: ነገር ግን ዕለቱ በዓል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ እስከ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታዉን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለፀው መሰረት የተጫረተበት ዕቃ ናሙና /Sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. ጥራት (Quality)በሌለው እቃ ላይ መስሪያ ቤቱ የማንደራደር መሆኑን በቅድሚያ እናሳውቃለን፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ ያለምንም ስርዝ እና ድልዝ በመሙላት ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ሰነድ ላይ ማኖር አለባቸው፡፡
  12. መቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የ "ሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114 45 01 82 ይደውሉልን፡፡ ኢድራሻ: በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገላን ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የገላን ከተማ
አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

 

Save Tender