Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Aug 2022, 10:51 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ የብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ ፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ ሌሎች አላቂ እቃዎች ፣ አላቂ የህክምና እቃዎች ፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣ ቋሚ እቃዎች ለመግዛት እና ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁፕር 1/2015

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ የብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከመንግስት ከተመደበለት መደበኛ እና የውስጥ ገቢ በጀት ለ2015 ዓ.ም. አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት እቃዎችን ለመግዛት እና ስፌት ማሰፋት ይፈልጋል።

በዚህም

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2 አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
  • ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
  • ሎት 4 ሌሎች አላቂ እቃዎች፣
  • ሎት 5 አላቂ የህክምና እቃዎች፣
  • ሎት 6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 7 ቋሚ እቃዎች ለመግዛት የሚፈልግ ስለሆነ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል

ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በኢፌድሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት ዉስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋት 2፡30-1፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን አሽገው ዋናዉን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታዉ እስከሚከፈትበት ቀን ከጠዋት 4:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላል። ጨረታዉ በ11ኛዉ በስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ፦

  • ተጫራቾች የተጫረቱበትን እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  • ተጫራቾች ውል ከመፈረማቸዉ በፊት የዉል ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምረዉ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ መሞላት አለባቸው።
  • ብርሀን በር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በጨረታው ከሚቀርቡት የእቃዎች ብዛት አሸናፊ ከሆነው ድርጅት እስከ 20% ድረስ ለመቀነስ ወይም ለመር ብት አለው።
  • ማንኛዉም ተጫራች ለናሙና /ለሳምፕል ያስያዘውን እቃዎች የጨረታ ውጤት ከተነገረ በኃላ 10 ቀናት ውስጥ መውሰድ አለበት ከዚህ ቀን ውጭ ዘግይቶ ለሚመጣ ተጫራች በቂ ማስቀመጫ ቦታ ስለሌለ ቢበላሽ አይጥ ቢበላው ሃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እናሳዉቃለን።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦ ዋናው ሰነድ ውስጥ ማስገባት አለበት።
  • ከተቋሙ የገዛችሁት የጨረታ ሰነዶች በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቶን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  • ጥቃቅን እና አነስተኛ የሆናችሁ ከምታመርቱበት ውጪ የምትወዳደሩ ከሆነ ሲፒኦ እና ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
  • ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡- አጠና ተራ ወረዳ10 ከተቃጠለው ህንፃ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0112792458 /0112739672

በዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ብርሃን በር

ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender