በም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2015 ሙሉ በጀት የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን ፣ የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ፣ ሞተር ሣይክል ፣ የደንብ አልባሳት ፣ የመኪና እና የሞተር ሣይክል ጐማዎች እና ከመነዳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2015 ሙሉ በጀት በወረዳ ደረጃ ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣
- የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- ሞተር ሣይክል ፣
- የደንብ አልባሳት ፣
- የመኪና እና የሞተር ሣይክል ጐማዎች እና ከመነዳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ ዕቃዎቹ የሚገልጽ ሰነድ/ዶክመንት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
የተጫራቾች ግዴታዎች፟፦
- ከግዥው ጋር ተያያዥነት ያለውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። በዚህም የሚጠበቅባቸውን የመንግስት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ ሕጋዊ የአቅራቢዎች ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ። እንዲሁም ያሸነፉበትን ዕቃዎች ለድርጅቱ ገቢ ሳያደርጉ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና ውሉን በወሰደ 05 ቀን ውስጥ ገቢ ማድረግ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ስራ አፈጻጸም የሚውል ወይም የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው አቅርቦት 10% በሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ።
- አሸናፊ ድርጅት ባሸነፏቸው ዕቃዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ ሁለት (2) ወር ማቆየት ይኖርበታ።
- ዕቃውን እስከ ወረዳው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜያቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም።
- ተጫራቾች ከነሐሴ 2/2014 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20/2014 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው 15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በዚያው ቀን ይከፍታል። ጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል። በዚህ ቀን 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኖኖ ወረዳ ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች በጨረታው መከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባይገኙ የጨረታው ሂደት አያስተጓጉልም።
- ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጨረታ ላይ እንዲሳተፋ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ 214 ኪ.ሜ. ላይ የሚገኝ ሲሆን በወልቂጤ መንገድ 216 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ትገኛለች።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር-011-884-7422/0913-76-85-30 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሥልክ- አምባ
