በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ ፣ የጽዳት እቃዎችን ፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2015 .ም በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች
- የጽህፈት መሳሪያ ፣
- የጽዳት እቃዎችን ፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን ፣
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣
- የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን እና
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች :
- በዚህ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው የ 2014/2015 የታደሰ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን እቃዎች ኩዩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል።
- ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሽግ በ16ኛዉ ቀን 7፡45 ሰዓት ላይ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000/ አስር ሽህ ብር/ በማስያዝ ከላይ በተጠቀሰው መ /ቤት ያስገባሉ።
- ጨረታው በ 16ኛዉ ቀን ከቀኑ 8፡20 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ይቻልም።
- ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የስራ ልምድና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0920 95 40 09 / 0911 77 56 00/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንስት መስተዳድር ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
