የምስ/ሐረርጌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ ፣ የጽዳት ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸሮች ፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 001/2015
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የምስ/ሐረርጌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች
- የጽህፈት መሳሪያ ፣
- የጽዳት ፣
- ኤሌክትሮኒክስ ፣
- ፈርኒቸሮች ፣
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈለና ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ
- በመንግስት ግዥ እቃ አቅራቢነት የተመዘገበና መረጃ ያለው
- በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ለጨረታ ማስከበሪያ በመስሪያ ቤቱ ስም ለአንድ ሎት 10,000 (አስር ሺህ ብር) CPO አሰርቶ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከምስራቅ ሐረርጌ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዢና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት በ4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾቹ ፋይናንሽያል የጨረታ ሰነዶቹን ኮፒውንና ኦርጂናሉን በተለያየ ፖስታ አሳሽገው ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡበት ሰነዶች (CPO) ጨምሮ በሶስተኛው ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0256 66 0137 ይደውሉ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የም/ሐ/ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
