በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስር ለሚገኙ ህግ ታራሚዎች የበሠለ ምግብ የሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል ለመፈፀም ይፈልጋል
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የበሰለ ምግብ አቅርቦት
በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስር ለሚገኙ ህግ ታራሚዎች የበሠለ ምግብ የሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል ለመፈፀም ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ተፈላጊውን የምግብ አይነት ብዛትና መጠን የሚገልጽ የጨረታ ሠነድና መመሪያ የማይመለስ ብር 100 በመከፈል ሠነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጀ ህጋዊ ማህበር እና ሌሎች የግል የምግብ አብሳዮች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ነጋዴዎች ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
- ምግብ አብስሎ ከማቅረብ ጋር በተያያዘ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- ህጋዊ የምስክር ወረቀት እና የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሸጣል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ ቀናት ብቻ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
- የበሰለ ምግብ አቅርቦቱ የሚያሸንፈው ጊዜ ለ6 ወር ይሆናል።
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ለዚህ ስራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዶክመንታቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ። ሌሎችም የምግብ አቅራቢዎች ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው መሳተፍ እንደሚችሉ ያሳስባል።
- ለተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር 025 666 0541 ፖስታ ሳቁ 31
የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
