Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Aug 2022, 10:38 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሸን ድርጅት አጠቃላይ የቢሮ ህንጻዉን ፣ አዳራሾችን ፣ ሻወሮችን ፣ መፀዳጃ ቤቶችን ፣ የአትክልት ቦታዎችን ፣ ንብረት ክፍሎችን ፣ መጋረጃዎችን እና ግቢዉን በሙሉ የግቢ ጽዳት አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉን አገልግሎት ሰጭ ተወዳዳሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


የቢሮ ፅዳት ግልጽ የጨረታ
ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB AWWCE 01/2014

የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሸን ድርጅት አጠቃላይ የቢሮ ህንጻዉን፣ አዳራሾችን፣ ሻወሮችን ፣መፀዳጃ ቤቶችን፣ የአትክልት ቦታዎችን ፣ንብረት ክፍሎችን፣መጋረጃዎችን እና ግቢዉን በሙሉ የግቢ ጽዳት አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉን አገልግሎት ሰጭ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀዉ መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1.  የዘመኑን ግብር ከፍለዉ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2.  የጨረታ ሰነዱን ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘዉ የአማራ ዉሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ አችን 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ዝርዝር የስራዉን መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ መመልከት የሚችሉ ሲሆን ለስራዉ የሚያስፈልጉ የሰዉ ሃይል፣ የማጽጃ መሳሪያ /ማቴሪያል/ እና ማንኛዉም ታክስ በራሱ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች በድርጅታችን ስም የተሰራ በሲፒኦ ወይም ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደ ተጠየቀ የሚከፈል /Unconditional Bid bond garantee/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 6,000,000 (ስድስት ሽህ ብር) ማስያዝ አለባቸው:: አሸናፊው ከተለየና ውል ከተፈረመ በኋላ ላላሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡
  4.  ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ጥቅል የጽዳት አገልግሎት ዋጋ የሚሸፍን ይሆናል ሌሎች ከጽዳት ጋር ተታያዙ ማንኛውም ወጪዎች በተሰጠው ዋጋ ላይ ተጠቃሎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የተሞላው ዋጋ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ለተገለፀዉ አገልግሎት የሚያቀርቡትን ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
  6. በጨረታው የሚቀርበው ዋጋ የወሩን እና የአመቱን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ሞልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይቻም ካለ ግን ዋጋውን በሞላው አካል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ባሕርዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  8.  ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ይከፈታል:: የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡

ለበለጠ

መረጃ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 058 222 14 79 /0983568731
መደወል ይችላሉ:: አድራሻ ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት
ለፊት
የአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሸን
ድርጅት

Save Tender