የመኖሪያ ቤትና ወርክ ሾፕ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ በቀለች ተፈራ እና በፍ/ባለዕዳ ራች ቴርዚያን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 68974 (23/7/2001 ዓ.ም. እና መ/ቁ 147889 በ16/3/2012 ዓ.ም. በ20/4/2012 ዓ.ም. እና 01/05/2012 ዓ.ም. 8/10/2014 ዓ.ም. ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሰበታ ከተማ ቀበሌ 02 በቀድሞ አለምገና ወረዳ ሰበታ ከተማ የሚገኝ ሪቭትሮፒክ ተብሎ የሚጠራ 3 መጋዘኖች 6 ክፍሎች መኝታ ቤቶች ከመጋዘኑ ጀርባ ያለው በሪቭ ትሮፒክ መናፈሻ ስም ካ/ቁ ሰ/26381/2002 የተመዘገበ ካርታ ያለው ስፋቱ 6704 ካ.ሜ. የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 7,113,298.87 (ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ሦስት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ከሰማኒያ ሰባት ሳንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ካፒታል ጌይን ከሽያጭ የሚከፈል መሆኑ ታውቆ ለጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
2ኛ በሰበታ ከተማ ቀበሌ 02 በቀድሞ አለም ገና ወረዳ ሰበታ ከተማ የሚገኝ በሚስተር ራች ቴራዚያን ስም ካ/ቁ ሰ/248/96 የተመዘገበ መኖሪያ ቤትና ወርክ ሾፕ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,888,722.50 (አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺ ሰባት መቶ ሃያ ሁለት ከሃምሳ ሳንቲም) ስፋቱ 5042.63 ካ.ሜ. ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል ሆኖ ለጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በ4:30 በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታከስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬከቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በኢፌዴሪ ጠ/ፍ/ቤት የፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
