Tender Detail

Tender Details

  • Company Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
  • Address ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 80 88
  • Websitehttps://dbe.com.et/
  • Deadline10 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 20% (ብር 12,998,349.59) CPO
  • opening dateህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Business, Industry And Factory Foreclosure

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ኪራይ ተከራዩ በውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል:

Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሰውን የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥ እና ኪራይ ተከራዩ በውሉ መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዩ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በሐራጅ አወዳድሮ በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይፈልጋል:

የካፒታል ዕቃ ተከራዩ ስም የሚሸጠው ንብረት የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ የሐራጅ ደረጃ ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት
አቶ ሀብታሙ አበጋዝ ኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን እና የተለያዩ ሲሊንደሮች 64,991,747.97 ቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ክ/ከ በተከራዩ የማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ 2ኛ በተከራዩ ማምረቻ ቅጥር ግቢ ውስጥ ህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4:00-6:00

ማሳሰቢያ:-

  1. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሽያጭ ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል፡፡
  3. ድርጅቶችን በመወከል በሽያጭ ጨረታ ላይ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠ ዋና የውክልና ስልጣን እና አስፈላጊ ሰነድ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
  6. የጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያ ጨምሮ ገዥው ይከፍላል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራች ማሽኑን ካለበት ማምረቻ ቦታ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባለቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል፡፡
  8. ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር:- 022-211-66-87 ላይ መደወል ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራች አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
Development Bank of Ethiopia, Adama District, is auctioning repossessed capital goods (an oxygen production machine and various cylinders) for cash. Bidders must submit a 20% CPO; the winner pays the balance plus 15% VAT within 15 days or forfeits the deposit. Agents must present verified power of attorney.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender