Tender Detail

Tender Details

  • Company Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
  • Address ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 80 88
  • Websitehttps://dbe.com.et/
  • Deadline17 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4 (ብር 2,113,160.35) CPO
  • opening dateህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Business, Industry And Factory Foreclosure

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ የናታን ምንተስኖት ለሰጠው የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪ ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በአግባቡ ባለመክፈሉ ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)


የመጀመሪያ ዙር የሃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ የናታን ምንተስኖት ለሰጠው የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪ ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በአግባቡ ባለመክፈሉ ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባለበት ሁኔታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ የንብረቱ አይነት ብዛት
1 Brade slicer (01) set
2 Rotary oven 14Tray
3 Dough mixer (01) set
4 Volumetric Dough Divider (01) set
5 Molding Machine (01) set
6 Flat tray with trolley (02) set
7 French tray with trolley (02) set
8 Diesel Generator 24kW (01) set
9 Proofer (01) set

ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ: በደ/ኢ/ክ/መ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ
የሃራጅ መነሻ ዋጋ በብር: 8,452,641.40
ሃራጁ የሚካሄድበት ቀን፣ ሰዓትና ቦታ: ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም፣ 4:00-6:00፣ በደ/ኢ/ክ/መ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ በማምረቻ ሼዱ ውስጥ

ማሳሰቢያ

  1. ከላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25) በመቶ 2,113,160.35(ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ከ35/100) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላል።
  2. ማሽነሪው የተተከለ ሲሆን የሚሸጠው ማሽኑ ብቻ በመሆኑ አሸናፊው ካሸነፈ በኋላ ማሽነሪውን ነቅሎ የመውሰድ ሃላፊነት ያለበት ሲሆን የማሽነሪውን መንቀያ እና የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈነው በአሸናፊው ነው።
  3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነፃ ስለሆነ ገዥው የቀረጥ ነፃ ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ይደረጋል፤ ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያውን ገዥው ይከፍላል።
  4. ሐራጁ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00-6:00 ሰዓት ይከናወናል።
  5. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በስሙ ለሚገዛ ባሸነፋት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያ ጨምሮ አሸናፊው ይከፍላል።
  6. አሸናፊው የሀራጁ አሸናፊ መሆኑ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ማሽነሪዎችን ለማስጠበቅ የሚከፈል ክፍያ ለማሽነሪዎች መጠለያ ኪራይ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎች የመክፈል ግዴታ አለበት።
  7. አሸናፊው የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት ካሟላ ሽያጩ በዱ.ቢ. ግዥ ይሆናል።
  8. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት ካልከፈለ ባንኩ የሐራጅ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሀራጁ በድጋሚ ይከናወናል። በድጋሚ ሲሸጥ የሚፈጠረውን የዋጋ ልዩነት ይከፍላል።
  9. ሀራጁ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-6:00 ንብረቶቹ በሚገኙበት በደ/ኢ/ክ/መ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ በሚገኘው የማምረቻ ሼድ ውስጥ ይከናወናል በሀራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተወዳዳሪ ሀራጁ ከሚካሄድበት ቀን የሀራጅ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ማለትም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሐራጅ ቦታ በመገኘት ምዝገባ ማካሄድ ሲ.ፒ.ኦ እና የታደሰ መታወቂያ ኮፒ ለጨረታው ኮሚቴ ማስረከብ አለበት።
  10. ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-181-06-06/03-03 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
  11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
Development Bank of Ethiopia, Arba Minch District, is auctioning bakery machinery (slicer, rotary oven, dough mixer, divider, molding machine, trays with trolleys, 24kW diesel generator, proofer) repossessed after the lessee defaulted on lease payments. Sold as-is; buyer bears dismantling and transport costs.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender