የአዳማ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ እና የአዳማ አትሌቲክስ ክለብ የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ እና የአዳማ አትሌቲክስ ክለብ የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1.ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች /የተጫራቾች መመሪያ/።
1.1 ማንኛውም ድርጅት ግለሰብ እና በዘርፉ የተሰማሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
1.2 ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው።
1.3 ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል አዳማ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 100014814136 በማስገባት ጨረታው ከወጣበት የሥራ ቀን ጀምሮ አዳማ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት መግዛት ይችላል።
1.4 ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለምግብ አቅርቦት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ ቼክ የተረገጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
1.5 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀን የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው የሥራ ቀን በ4:00 ሰዓት ታሸጎ በዚሁ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም። ሆኖም 16ኛው ቀን በዓል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
1.6 ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒውን እና ኦሪጅናሉን በተናጠል በማቅረብ አዳማ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በመቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀን ማስገባት ይችላሉ።
1.7 የምግብ ዝግጀት ቦታ የሴቶች እና የወንዶች በካንፓቸው ለ90 ስፖርተኞች መመገብ የሚችል ሆኖ ለሀ-17 እና ለሀ-20 በአሸናፊው ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ 60 ሰው እና ከዚያ በላይ መመገብ የሚችል ደረጃውን የጠበቀ አዳራሽ ውስጥ ማዘጋጀት የሚችል እና ለቅድመ ጨዋታ መሰብሰቢያ እስከ 25 ሰው መያዝ የሚችል አዳራሽ ያለው መሆን አለበት። ለአትሌቲhስ ከለብ በአሰላ ካምፕ ለ89 አትሌቶች መመገብ የሚችል መሆን አለበት።
1.8 ለስፖርተኛ ምግብ በሚዘጋጅበት አዳራሽ ውስጥ ከአልኮል መጠጥ፣ ከተለያዩ ሱስ አስያዥ፤ ዕፆች፣ ጭፈራ ቤት እንዲሁም ስፖርተኛን ሊረብሹ የሚችሉ የፋብሪካ ድምፅ የራቀ መሆን አለበት።
1.9 ተጫራቾች በቂ የማድቤት እና የምግብ ቁሳቁስ ከበቂ የሰው ኃይል ጋር ያለው መሆን ይጠበቅበታል።
1.10. ተጫራቾች በ2014 ዓ.ም. በዚህ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው እየሠሩ ያሉ መሆኑን የሚገልፅ የሥራ ልምድ ከንግድ እና ገበያ አገልግሎት ጽ/ቤት እና ሲሠሩ ከነበረበት ቦታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
1.11. ሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
የአዳማ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ክለብ
