Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Jul 2022, 2:38 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች ፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።



በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 40/2014

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ  ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ሞተር ሣይክ ሎች የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተሽከርካሪዎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ  ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር 7. በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:00 እስከ 6:00፣ ከሰዓት ከ7:00 እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ  ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO፣ የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 7ኛው (ሰባተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8ኛው (ስምንተኛው) ቀን የግልፅ ጨረታ ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡05 ሰዓት ማዕከላዊ መጋዘን ይካሄዳል:: ነገር ግን ጨረታው በበዓል (እሁድ) ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  5. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫት እና ያለቫት በሚል በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መል በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋቅ ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም::
  6. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
  9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ኮሚሽኑ ተጠያቂ አይሆንም::
  11. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው::
  12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀና ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል ይህንን ባያደርጉ ጨረታ ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁፕር -046 212 5396

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ፅቤት

Save Tender