Tender Detail

Tender Details

  • Company የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት (Nedi Gibe Woreda Roads and Logistics Office)
  • Address Dimtu town, Nedi Gibe Woreda, South West Oromia Zone, Oromia, Phone: 0924437559
  • Website
  • Deadline07 Dec 2026, 12:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityብር 500,000 CPO
  • opening dateበዚያው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Sector Construction , Road and Bridge Construction , Rent , Machinery and Equipment Rent

የደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶችና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ሻወር ትራክና ገልባጭ ማሽነሪዎችን ለመከራየት በድጋሚ ያወጣው ጨረታ።

የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት (Nedi Gibe Woreda Roads and Logistics Office)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብ/ክ/መ በደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በ2019 ዓ.ም ለሚያከናውነው የተለያዩ መንገዶች ግንባታና ጥገና ማሽነሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ የወረዳው መንገዶችና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት በሚያወጣው የጨረታ መስፈርት እና ደንብ መሰረት መጥታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የማሽነሪዎቹ አይነት

  1. ዶዘር CAT D8R
  2. ግሬደር SANY STG-230
  3. ኤክስካቫተር CAT 330 DL, CL
  4. ሮለር 16 Ton
  5. ሎደር
  6. Shower Truck 16m3
  7. ገልባጭ 14 m3

ሲሆኑ አመልካቾች

  1. ህጋዊ የማሽን ማከራየት ፍቃድ ያላቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና ቲን ቁጥር ያላቸው
  3. የ2019 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ
  4. የማሽነሪዎቹ ሞዴል 2016 G.C እና ከዚያ በሁዋላ መሆን አለበት
  5. ከዚህ በፊት በሰሩበት የመልካም አፈጻጸም ምስክር ወረቀት ያላቸው
  6. የማሽነሪዎችን ማስጫኛና ተያያዥ ወጪዎች በራሳቸው መሸፈን የሚችሉ ሆኖ በሚያቀርቡት የማሽነሪዎች ዋጋ ውስጥ ታሳቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቀርበው የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 500,000 በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የቅድመ ማጣሪያ ቴክኒካል ዶክመንት በጥንቃቄ በመሙላት እና አስፈላጊ ዶክመንቶችን በማያያዝ ኦርጅናል፣ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ (CPO) ለየብቻ በማሸግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሶስቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ ማሸግ እና ቴክኒካል ዶክመንት በማለት መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል) ዶክመንት ኦርጂናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ተገቢውን መረጃ በፖስታዎቹ ላይ በጉልህ በመጻፍ ሁለቱንም በሌላ ኤንቨሎፕ በማድረግ፣ በመጨረሻም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል አንድ ላይ በሌላ ኤንቨሎፕ በማሸግ አስፈላጊውን መረጃ በጉልህና ግልጽ በሆነ ጽሁፍ በመጻፍ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከቀኑ 6:30 ሰዓት ድረስ ብቻ በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ6:30 ተዘግቶ ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ውስጥ በይፋ ይከፈታል
  12. ስርዝ ድልዝ ያለባቸውንና በግልጽ የማይነበቡ አሻሚ ፊደሎች ያላቸው እንዲሁም የማይነበቡ ሰነዶች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የላቸውም

ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጮችን ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ ዞን ነዲ ጊቤ ወረዳ ዲምቱ ከተማ
ለተጨማሪ መረጃ - 09 24 43 75 59 አልያም በወረዳው መንገዶች ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በኦሮሚያ ብ/ክ/መ በደቡብ ምእራብ ኦሮሚያ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ መንገዶች እና ሎጅስቲክ ጽ/ቤት

Summary
Nedi Gibe Woreda Roads and Logistics Office (South West Oromia zone) re-tenders the rental of road machinery: a CAT D8R dozer, a SANY grader, a CAT 330 excavator, a 16-ton roller, a loader, a shower truck and a dump truck, all 2016 models or newer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender