የካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሹኒቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የመናኸሪያ ዙሪያ አጥር፣ የአደባባይ፣ የኮንቴነር/ሼድ እና የውሃ መስመር ጥገናና አዲስ ስራዎችን በ4 ሎት ለማሰራት BC/GC/WC ደረጃ 7 እና 9 ተቋራጮችን የጋበዘበት ግልጽ ጨረታ (ቁጥር ግ 003/19)።
የደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ግ 003/19
በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን በጌሻ ወረዳ የሹኒቲ ማዘጋጃ ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል በጀት የተለያዩ ግንባታዎችን በሎት ከፋፍሎ ለማስገንባት ፈልጎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት
| ተ.ቁ | የግንባታዉ ዓይነት | የስራ ቦታ | ሎት | መረጃ | CPO | ደረጃ |
|---|---|---|---|---|---|---|
| 1 | መናኸሪያ ዙሪያ አጥር | ሹኒቲ | 01 | B.C ወይም G.C | 30000 | ዘጠኝ (9) እና ከዚያ በላይ |
| 2 | አደባባይ ሎት | ሹኒቲ | 02 | B.C ወይም G.C | 1200 | ዘጠኝ (9) እና ከዚያ በላይ |
| 3 | ኮንቴነር /ሼድ/ ስራ | ሹኒቲ | 03 | B.C ወይም G.C | 4400 | ዘጠኝ (9) እና ከዚያ በላይ |
| 4 | የውሃ መስመር ጥገናና በኖ ስራ | ሹኒቲ | 04 | W.C ወይም G.C በውሃ ግንባታ | 7300 | ዘጠኝ (9) እና ከዚያ በላይ |
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
- ሎት 01 ደረጃ ሰባት (7) እና ከዚያ በላይ ሎት 02 እና ሎት 03 ደረጃ ዘጠኝ (9) እና ከዚያ በላይ የሆነ / B.C ወይም G.C/ ሎት 04 ደረጃ ዘጠኝ (9) እና ከዚያ በላይ የሆነ / W.C ወይም G.C በውሃ ግንባታ/ ህጋዊ የግንባታ ፍቃድ ያለዉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- ቫት ተመዝጋቢነት መረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ህጋዊ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለመንግስት 3 በመቶ ታክስ ከሚያገኘዉ ገቢ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፣
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ሰላሳ /30/ የስራ ቀናት ዉስጥ በጌሻ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ከፍል ተጫራቾች ለግንባታዉ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል የጨረታዉን ሰነድ በመግዛት ቴክኒካል ኦርጅናል ብቻ፣ ፋይናንሻል ዋናዉንና ሁለት ኮፒዉን ለየብቻ የግንባታዉን ስም በመለየት በታሸገ ኤንቬሎፕ የድርጅቱን ስም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛ ቀን እስከ 3:00 ሰዓት ድረስ በጌሻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት የቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቹ ድርጅቱ አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆነ
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ስራ ሂደት ቢሮ በ31ኛዉ ቀን 3:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ያለመገኘት ጨረታዉን አያስተጓጉልም፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በሰንበት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለዉ የስራ ቀን ተላልፎ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ለሎት 01 ብር 30000 ለሎት 02 ብር 1200 ለሎት 3 ብር 4400 ለሎት 04 ብር 7300 በባንክ በተረጋገጠ የክፊያ ትዕዛዝ CPO በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
Summary
Gesha Woreda Finance Office (Kaffa zone, South West Ethiopia) invites BC/GC/WC contractors for four municipal works in Shuniti town: a bus station perimeter fence, a public square, a container shed, and water line repair and extension.
