በአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ከአማራ ክልል መልሶ ማቋቋም ግንባታ ልማት ፈንድ በተገኘ በጀት የተለያዩ የእንስሳት ጤና ክሊኒክ እና የማር ሙዚየም ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:-እ/አ/ሀ/ል/ቢ/ግጨ01/08/19
በአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ከአማራ ክልል መልሶ ማቋቋም ግንባታ ልማት ፈንድ በተገኘ በጀት የተለያዩ የእንስሳት ጤና ክሊኒክ እና የማር ሙዚየም ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር {TIN} ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ {VAT} ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ግንባታ የሚከናወንባቸው ቦታዎች ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ተገልፀዋል::
| ሎት | የፕሮጀክቱ/ የግንባታ/ ስም | ዞን | ወረዳ | ቀበሌ | ተፈላጊ ደረጃ GC/BC Grade | የጨረታ ማስከበሪያ መጠን. ብር | ሰርቶ የማጠናቀቂያ እና የማስረከቢያ ጊዜ (ወር) |
| 1 | ጭልጋ 1 እና 2 የእንስሳት ጤና ክሊኒክ | ማዕከላዊ ጎንደር | አዲሱ ጭልጋ እና ነባሩ ጭልጋ | 5 እና ከዚያ በላይ | 360,000 | 6 | |
| 2 | ደብረ ኤልያስ እና ፍኖተሰላም የእንስሳት ጤና ክሊኒክ | ምዕራብ ጎጃም እና ምስራቅ ጎጃም | ደብረ ኤልያስ እና ፍኖተ ሰላም | 5 እና ከዚያ በላይ | 240,000 | 6 | |
| 3 | ቃሉ የእንስሳት ጤና ክሊኒክ | ደቡብ ወሎ | ቃሉ | 5 እና ከዚያ በላይ | 144,000 | 6 | |
| 4 | ላሊበላ ንብ ማግባር ማሰልጠኛ እና ሙዚየም | ሰሜን ወሎ | ላሊበላ | 5 እና ከዚያ በላይ | 340,000 | 6 | |
| 5 | ወልቃይት የዳልጋ ከብት ዝር/ማሻ/ ማዕከል | ወልቃይት ጠገ/ሴ/ሁመራ | ሁመራ | ማርዉሃ | 5 እና ከዚያ በላይ | 340,000 | 6 |
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ባለው ሰንጠረዥ በየሎቱ በጠጠቀሰው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ መይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከቴክኒካል ዶክመንቱ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያየ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሀሳብ በማለት ማቅረብ አለባቸው።
- ለቴክኒካዊ ብቃት መስፈርቶች ከተመደበው ጠቅላላ ነጥብ ቢያንስ 70% ማምጣት ያልቻሉ ተጫራቾች ለቀጣዩ የፋይናንስ ግምገማ አይታዩም፤ እንዲሁም የዋጋ (ፋይናንስ) ሀሳብ ሰነዶቻቸው ሳይከፈቱ ይመለስላቸዋል። የተመረጠው የአሸናፊ መለያ ዘዴ "ዝቅተኛ ዋጋን መሰረት ያደረገ ምርጫ" (Least Cost Selection) ነው::
- ከአንድ በላይ በሆኑ ሎቶች (Lots) ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች፤ ለእያንዳንዱ ሎት የሚሆኑ የተለያዩ ቁልፍ ባለሙያዎችን፤ማሽነሪዎችን፤ልምድ እና ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ማቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች ቀደም ሲል የነበሩ ውሎችን በአጥጋቢ ሁኔታ መፈጸማቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ከዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች (ወረዳ ወይም ዞን) የተገኙ የፕሮጀክት ሥራ ልምድ ሰነዶች በክልል ደረጃ በሚገኝ አግባብነት ያለው አካል መረጋገጥ (ማረጋገጫ ማግኘት) አለባቸው። በክልል ደረጃ የተሰጠ ይህ ማረጋገጫ የሌለው የሥራ ልምድ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤ እንዲሁም ለቀጣይ ግምገማ አይታይም።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 2:30 እስከ 6:30 ከሰዓት ከ 7:30 እስከ 11:30 የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ጨረታ ሰነድ የወሰዱ ተወዳዳሪዎች የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ፤ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው ከ18/03/2019 ዓ.ም እስከ 07/04/2019 ዓ.ም በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ 08/04/2019 ዓ.ም ዓ.ም ከጧቱ 3:30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል ::ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ይከፈታል ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0583207434/0583201523 በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ::
- አድራሻ:- ባህር ዳር ቀበሌ 3 አብክመ ግብርና ቢሮ ጎን
አብክመ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ቢሮ
ባህር ዳር
Summary
Amhara Livestock and Fishery Resource Development Bureau invites grade 5+ GC/BC contractors to build animal health clinics, a beekeeping training center and honey museum, and a cattle breeding center in five lots.
