የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለመንገድ የመሬት ላይ ሥራ የዶዘር ማሽን ኪራይ
Wayu Tuka Woreda Finance Office
የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዋዩ ቱቃ ወረዳ መንገዶች ባለ ሥልጣን ጽ/ቤት ለአዲስ መንገድ የመሬት ላይ ሥራ/ Earth Work) ለ2019 በጀት ዓመት ለማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሽነሪዎች ሥራው በሚሰራበት ቦታ ጭኖ ማድረስ ለሚችልና እያንዳንዱን ማሽነሪ በሰዓት በስንት አከራይቶ እንደሚሰራ በመግለጽ ለመወዳደር ለሚፈልግ ሰው የማሽኑን ዓይነት እንደሚከተለው እንገልጻለን ::
1. Doozera (ዶዜራ) ሞዴላ CAT D8- R
- የስሪት ዘመን 2014 እና ከዚያ በላይ
- የፈረስ ጉልበቱ 305 እና ከዚያ በላይ የሆነ
- ለ 1 ሰዓት የሚሰራበት ዋጋ
- ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከለለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብር 30,000 (thirty thousand) ሰርቪሱን፤ ነዳጁን ፤ የኦፕሬተርና የረዳት ደመወዝና አበል ችሎ እንደዚሁም የትራንስፖርት ሎቤዳ ዋጋ ( Loobeda) ጨምሮ ለመሥራት የሚችል ከዚህ በታች ያሉትን ምዘናዎችን ለሚያሟላ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል::
በመሆኑም:-
1.የ2018 ዓ/ም የንግድ ግብር የከፈሉና 2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
2.ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ የንግድ ዘርፍ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
3.የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
4.በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5.ተወዳዳሪው ሊብሬው የራሱ ወይም ሕጋዊ ውክልና ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ከዶክሜንቱ ጋር ማቅረብ የሚችል
6.የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ/ቢድ ቦንድ /በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ለማሽኑ ኪራይ 1 % ማቅረብ አለበት
7.ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ በጊዜ ሠርተው ማቅረብ የሚችሉ
8.አስተማማኝና ጥራት ለሌላቸው ሥራዎች ተጠያቂነትን የሚወስዱ
9.ካሁን ቀደም በተለያየ ቦታ ለመሥራታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ / ከ2014 -2019/
10.አንዱ ተጫራች በሚያቀርበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር የማይቻል መሆኑን
11.ማሽኑን ከአንድ የመስመር ቦታ ወደ ሌላ የመንገድ ሥራ መስመር ማሽኑን በራሱ ወጪ ማጓጓዝ የሚችል
12.በሥራ ላይ ብልሽት ቢያጋጥም አንድ ቀን በማይበልጥ ጊዜ ዉስጥ ማሰራት የሚችል
13.ተወዳዳሪዎች የተጠየቁትን ማስረጃ በሙሉ 1. ቴክኒካል ኦሪጂናሉንና ፎቶኮፒውን በሰም በታሸገ ለየብቻ በማድረግ ሁለቱን በአንድ በኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ፤ እና 2. ፋይናንሻል ኦሪጂናሉንና ፎቶኮፒውን በሰም በታሸገ ለየብቻ በማድረግ ሁለቱን በአንድ በኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ ወስጥ በማድረግ፤ ፋይናንሻል እና ቴክኒካሉን ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም/ በኤንቨሎፕ በታሸገ ውስጥ በማድረግ፤ ስም አድራሻ ማሕተምና ፊርማ በማድረግ
14.18/03/2019 - 30 /04 /2019 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን ከዋዩ ቱቃ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን መ/ቤት በመግዛት በመንግሥት የሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ::
15.ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሸነፉ ከታወቀ ባንክ (ኢንሹራንስ) 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ ለማቅረብ የሚገደዱ ይሆናል::
16. ከግዥው ዋጋ ሶስት እጅ ላይ አንድ እጅ አድቫንስ ጋራንት ዋስ ማቅረብ አለበት::
15.ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ብር 30,000/ ሰላሳ ሺህ)_ የማይመለስ ለዋዩ ቱቃ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን በመክፈል መግዛት ይችላሉ
17. ይህ ጨረታ የሚከፈተዉ ተወዳዳሪዎች ፣ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ወይም እነርሱ በሌሉበትም በ30/04 /2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4:00 ገብቶ በ 4:30 ላይ ዉድድሩ በወረዳዉ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1 ይካሄዳል::
18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ :- ተጨማሪ መረጃ ከሚሸጠው ሰነድ ማገኘት ይቻላል::
ስለ ጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ
09-11-45-99-68
09-11-95-43-57
09-53-28-46-06
