የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በኮሪደር ልማት የተገነቡ 43 የንግድ ሱቆች፣ የባንክ/ኢንሹራንስ ቢሮ፣ የካፍቴሪያ፣ የስፖርት ማዘውተሪያና የህፃናት መጫወቻ ቦታዎችን በ4 ምድብ ለማከራየት ያወጣው የኪራይ ጨረታ።
የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት (Arba Minch City Municipality)
የኮሪደር ንግድ ቤት የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የአ/ም/ከ/ፋ/ፕ/ል/መምሪያ፣ የአ/ከ/አስ/ጽ/ቤት ያስገነባቸውን የተለያዩ ለንግድ አገልግሎት የሚሆኑትን የኮሪደር ግንባታዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ሠነዱን በመግዛት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
| ተ.ቁ | የክራዩ አገልግሎት መግለጫ | CPO የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
|---|---|---|
| 1 | በኖክ ሳይት ኮሪደር ገበያ ማዕከል አገልግሎት የሚውል 43 (አርባ ሶስት) የንግድ ሱቆችና ሼዶች ኪራይ | 10,000.00 |
| 2 | በኖክ ሳይት ኮሪደር ለባንክ /ለኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሆን ቢሮ ኪራይ | 50,000.00 |
| 3 | በሼፍ ኢዛና ኢንተርናሽናል ሆቴል ለካፍቴሪያ፣ ስፖርት ማዘውተሪያ እና የህፃናት መጫወቻ የሚሆን ኪራይ | 50,000.00 |
| 4 | በኖክ ሳይት ኮሪደር ለካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል | 50,000.00 |
- ለመወዳደር በተፈቀደ ዘርፍ ብቻ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ወይም የንግድ ፍቃድ ለማውጣት ፍቃደኛ የሆኑ፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ከአርባ ምንጭ ከተማ ንግድ ገበያ መምሪያ ያወጣ እና ለማውጣት ፍቃደኛ የሆነ፣
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ 1500 ብር በባንክ ከፍለው የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የባንክ ስሊፕ ይዞ በመቅረብ በአ/ምንጭ ከተማ ፋይናንስ፣ ፕላንና ልማት መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ገዝተው በመመልከት መወዳደር ይችላሉ
- የጨረታው ሳጥን ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ የሚታሸግ ሲሆን በዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ኦርጅናል፣ የንግድ ፍቃድ ምስክር ወረቀት ኮፒ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ፣ TIN number ወይም የንግድ ፍቃድ ለማውጣት ፍቃደኛ የሆኑበትን ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አንድ ተጫራች የሱቁን አንድ ካሬ የሚገዛለትን ዋጋ የሚይዝ ሰነድ አያይዞ ማቅረብ አለባቸው ከላይ በተ.ቁ 6 የተገለፀ መረጃዎችን፣ ፋይዳ መታወቂያ እና ለጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የፋይናንሻልና የቴክኒካል ዶክመንት ለይተው በፖስታ በማሸግ በእናት ፖስታ አድርገው በከተማ ፋይናንስ፣ ፕላንና ልማት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ያስፈልጋል፣
- አንድ ተጫራች ከአንድ ሱቅ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ ተጫርቶ ከተገኘ ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ጨረታው የሚዳኘው በዚህ ማስታወቂያና በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀ መመሪያዎች መሠረት ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት
Summary
Arba Minch City Municipality rents out new corridor-development premises: 43 shops and sheds in a market center, a bank or insurance office, cafeteria space, and a cafeteria, sports and children play area at a hotel site.
