Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
  • Address አዲስ አበባ ሬስቶራንት ወረድ ብሎ የአራዳ ከ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ የመ/ደ/ት/ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1 26 62 73
  • Website
  • Deadline07 Dec 2026, 8:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ
  • opening dateበ11ኛው የስራ ቀን ከ 4:15 ሰዓት ጀምሮ
  • Sector House and Building , House and Building Maintenance , Maintenance and Repair

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደርጃ ትምህርት ቤት የሊያሰራው ለፈለገው ጥገና ስራ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል::

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ተቋ 002/2019 ዓ.ም

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደርጃ ትምህርት ቤት የሊያሰራው ለፈለገው ጥገና ስራ ላይ የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል:: በመሆኑም ለግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የሰው ሃይል በማቅረብ የሚሰሩ በጥቃቅን አነስተኛ ዘርፍ በ ጥቃቅን አነስተኛ ሙብቃት ማህበራትን በግል ጨረታ በማወዳደር ለማሠራት ይፈልጋል::

ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

ሎት የስራዉ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደረጃ የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን የጨረታ ማስገቢያ ቀን የጨረታ መከፈቻ ቀን
ሎት 1 የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አ/መ/ደ/ት/ቤት ጥገና ሥራ ከተደራጁበት ወረዳ የዋስትና ደብዳቤ በጥቃቅን አነስተኛ ሙብቃት በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት 2:30-10:00 ሰዓት በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:00 ድረስ ብቻ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከ 4:15 ሰዓት ጀምሮ
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ህጋዊ ዶክሜንታችሁን ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
  2. በዘርፉ የ2018/19 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና፣ ከስራ ከህሎት ቢሮ የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  4. ማንኛውም ስራ ተቋራጭ ከአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ እና ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይዝ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2:30 እስከ 10:00 ድረስ ከተራ ቁ.1-4 ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናዉን(orginal) እና የማይመለስ ቅጂ(copy) ይዞ በመቅረብ በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አ/መ/ደ/ት/ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  6. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4:00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:15 የሚከፈት ይሆናል።
  7. ማንኛውም ተጫራች የቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ያለበት በቴክኒካል ኦርጂናል ሰነድ ውስጥ ወይም ከፖስታው ውጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. አሰሪው መ/ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ የስራ መጠን 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይቻላል::
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾችን መመሪያ(Instruction Bidder(ITB) እንዲያነቡና የግንባታ ሳይቱን እንዲመለከቱ ይመከራል።
  10. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፤ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ። በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ፕሮጀክት አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የጨረታው ፋይናንሻል ሰነድ ላይ ያልተፈረመ ሆኖ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የተስተካከለ ዋጋ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ያሰርዛል። በተጨማሪም በስራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የስራ አይተም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
  11. ተጫራቾች የሥራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን አስፍሮ ማህተም በማድረግ ኢንቨሎፑን በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃትምህርት ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4:00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  12. አሸናፊ ተጫራች በስራ ዝርዝር ላይ ከገበያ ዋጋ በጣም ከፍ ያለ እና ዝቅ ያለ ዋጋ ከሞላ (Cost Break Down) ያቀርባል።
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የድርጅቱ የስራ ልምድና ማንኛውም በቴክኒካል የተጠየቁት ዶክመንቶችን አሰሪ መ/ቤት ኦርጂናል ዶክመንት ከሰጠው አካል የማጣራት መብት የተጠበቀ ነው።
  14. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:15 ጀምሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃትምህርት ቤት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
  15. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደጃች ውቢ በሚገኘው የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ፍይናንስ ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ ወይም 0111266273/0111565706 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር በወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 05 የትምህርት ብልጭታ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

Summary
Temhirt Bilchita Primary and Middle School (Arada, Woreda 05) re-advertises a bid for school repair works, open only to organized micro and small enterprises.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender