Tender Detail

Tender Details

  • Company Hawassa City Administration
  • Address Hawassa, Ethiopia, Phone: +251462205526
  • Websitehttps://www.hawassa.gov.et
  • Deadline07 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityበየሎቱ ብር 100,000 CPO ወይም ቢድ ቦንድ
  • opening dateበዚያው ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት፣ ቢሮ ቁጥር 54
  • Sector Gardening And Landscaping , Machinery Rental

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በዳካ፣ ታቦር፣ ሻፌታ እና ሀይቅ ዳር ክፍለ ከተሞች የኮሪደርና አረንጓዴ ልማት ቦታዎችን በቦቴ ውሃ የሚያጠጡ 13 ቦቴዎችን በ4 ሎት ለመከራየት ያወጣው ግልጽ ጨረታ።

Hawassa City Administration

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ልማት መምሪያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ለከተማ ጽዳት አስተዳደር አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት በከተማ ውስጥ ያሉ ግሪንሪዎች በቦቴ ውሃ ማጠጣት ስራ የኮሪደር ልማት አካል ሆኖ የተሰራውን ግሪነሪ ውሃ የሚያጠጡ 13 (አስራ ሶስት) ቦቴዎችን በ4(አራት) ሎቶች ተመድበው የሚሰሩ ስራዎች በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አወዳድሮ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት፡-

  1. ዳካ ክ/ከተማ አጠቃላይ ነባር አረንጓዴ ልማትና ኮሪደር ከጥቁር ውሃ ሳውዝ ስፕሪንግ ሎት/ምድብ 01(አንድ)
  2. ታቦር ክ/ከተማ ነባር አረንጓዴ ልማት እና ሜምቦ ሪፈራል ኮሪደር ሎት/ምድብ-02(ሁለት)
  3. ሻፌታ ክ/ከተማ ነባር አረንጓዴ ልማትና አዲስ ኮሪደር አረንጓዴ ልማት ሎት/ምድብ-03(ሶስት)
  4. ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ኮሪደርና ኤስ ኦ ኤስ ከብት እርባታ መንገድ ዳርቻ ግራና ቀኝ እና መንገድ አካፋይ ሎት/ምድብ-04(አራት)

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡- በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች፤-

  1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና
  3. የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
  5. በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፣
  6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ልማት መምሪያ ቢሮ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል ሰነዶችን አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አስር) ተከታታይ ቀናት በፋ/ኢ/ልማት/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አስፈላጊ የሆኑ ቴክኒካል ጉዳዮች በሚሸጥ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የሚገመገም ስለሆነ በጥንቃቄ መዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡
  10. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. በጨረታ ማስታወቂያ እና በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጣረስ ሁኔታ ካለ፣ የጨረታ ሰነዱ በላይነት ይኖረዋል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡ 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ

Summary
Hawassa City Administration Finance and Economic Development Department seeks licensed suppliers to rent 13 water tanker trucks, in 4 lots, to water corridor and green areas in Daka, Tabor, Shafeta and Hayk Dar sub-cities.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender

በጉለሌ ክ/ከተማ የሠላም ጤና ጣቢያ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የመኪና ኪራይ፣ ህትመት፣ ሪኤጀንትና...

READ MORE