በሸገር ከተማ አስተዳደር የለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ገልባጭ ሲኖትራክና ሮሎ ማሽነሪዎች ኪራይ ያወጣው ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ።
Lege Tafo Lege Dadi Sub City Finance Office
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር በኤካ ጣፎ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ለመጀመሪያ ዙር ለማዘጋጃ ጽ/ቤት ማሽነሮች ኪራይ (ማለትም ዶዘር፣ግሬደር፣ኤክስካቫተር፣ሎደር፣ ገልባጭ ሲኖትራክ፣ሩሎ ብቃት ያላቸውን ግለሰቦች እና ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ ማስረጃዎች በማቅረብ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ተመዝጋቢ የሆኑ።
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት እና በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,500(አንድ ሺ አምስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ አካውንት ቁጥር 1065018620317 በማስገባት/በመክፈል የኤካ ጣፎ ክ/ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ሰነዱን ከኤካ ጣፎ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር(ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ(ፖስታ) በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ድረስ በኤካ ጣፎ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በ16(አስራ ስድስተኛው) ቀን በ4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ(ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ በተገኙበት በኤካ ጣፎ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።ነገር ግን ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪላቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሚያቀርቡት ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ብር ዋስትና(CPO) ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO(ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል።
- የተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው ውል ካልፈፀሙ እና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታውን ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቶ መሄድ አይችልም።
- የመወዳደሪያ ጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሰረት ተሞልተው ማቅረብ ይኖርበታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0910325519/ 0933042930 በመደወል እና በአካል ተገኝቶ ማስረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች መንቀሳቀስ ለማይችሉ ማሽነሮች ሮሎ፣ሎደር እና እስካቫተር በክ/ከተማችን ውስጥ በአካል ቀርባችሁ ሰርቪስ ማድረግ ይኖርባቸዋል።ሌሎቹን ማሽነሪዎች እና መኪናዎች ግን በጋራዦቻችሁ ሰርቪስ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር በኤካ ጣፎ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
በሸገር ከተማ አስተዳደር የለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Summary
Legetafo Legedadi Sub-City Finance Office (Sheger City, Oromia) rents construction machinery for its municipality: dozer, grader, excavator, loader, Sinotruk dump trucks and roller. Licensed rental providers with TIN and tax clearance may bid.
