Tender Detail

Tender Details


የካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ፣ የውሃ ጥገናና የግንባታ ሥራዎች

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በካፋ ዞን የሳይለም ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/በካፋ ዞን የሳይለም ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2019ዓ.ም በጀት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል :- የኤሌክትሮኒክስ ግዥ፣የጽህፈት መሳሪያ ግዥ፣ የፈርኒቸር ግዥ ፣ጀኔሬተር ግዥ፣CBC ማሽን ግዥ ፣ኤሌክትሮ[...] ማሽን ግዥ፣ ማይክሮስኮፕ ማሽን ግዥ፣የውሃ ፓምፕ ጥገና ፣የውሃ ታንከር ጥገና፣ የውሃ ዕቃ ግዥ፣ የአዲስ ምንጭ ግንባታ ፣የእጅ ፓምፕ ጥገና ፣ በከተማ ውስጥ ካልቨርት ግንባታ ፣ዲ.ሽ ቢዩ ግንባታ ፣ የቆጠባ ቤት ግንባታ ፣የአደባባይ ግንባታ ፣የፓርኪንግ ግንባታ ፣ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ እና በዋን ዋሽ ሽንትቤት ግንባታ እና የእጅ ፓምፕ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት:-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች
  3. የግብር ከፋይ መለያ መረጃ ቲን እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
  4. የግዥውን 3% መቁረጥ የሚችል/የምትችል
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100/መቶ ብር/በመክፈል ካፋ ዞን የሳይለም ወረዳ ፋ/ይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ቀርበው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የግንባታ ወይም ኮንስትራክሽን ሲሆን በዚሁ ዘርፍ ቀደም ሲል ወረዳው በ2016-2018ዓ.ም በወጣው ጨረታ ተሳትፎ ግዴታቸውን በአግባቡ ስለመወጣታቸው የመልካም አፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. የዋን ዋሽ ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ነባር ተጫራቾች በተመለከተ በ2016-2018ዓ.ም ጨረታ ተሳትፎ በጊዜና በጥራት ስለመሥራታቸው ከት/ትና ከጤና ተቋማት መልካም አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል ።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካፋ ዞን የሳይለም ወረዳ ፋ/ይ/ጽ/ቤት በ2019ዓ.ም በጀት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል :-የኤሌክትሮኒክስ ግዥ 10,000/አስር ሺህ ብር/ ፣የጽህፈት መሳሪያ ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ፣የህንፃ መሳሪያ ግዥ5,000/አምስት ሺህ ብር/ ፣ፈርኒቸር ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/፣ጀኔሬተር ግዥ20,000 /ሃያ ሺህ ብር፣C-BC ማሽን ግዥ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣ኤሌክትሮ[...] ማሽን ግዥ 20,000.00/ሀያሺህ ብር/፣ማይክሮስኮፒ ማሽን ግዥ 20000.00/ሀያ ሺህ ብር/ ፣የውሃ ፓምፕ ጥገና 5,000/ አምስት ሺህ ብር/ ፣የውሃ ግንባታ 5,000/አምስት ሺህ ብር/ ፣ የውሃ ታንከር ጥገና 5,000/ አምስት ሺህ ብር ፣ የውሃ ዕቃ ግዥ 5,000/አምስት ሺህ ብር/ ፣ የውሃ ጥገና 5,000/ አምስት ሺህ ብር/ ፣በከተማ ውስጥ ካልቨርት 5,000/አምስት ሺህ ብር/፣ ዲ.ሽ ቢዩ ግንባታ 5,000/አምስት ሺህ ብር /የቆጠባ ቤት ግንባታ 10,000/አስር ሺህ ብር/ ፣የአደባባይ ግንባታ 10,000/አስር ሺህ ብር/ ፣የፓርኪንግ ግንባታ10,000/አስር ሺህ ብር/ ፣የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ 30000.00/ሰላሳ ሺህ ብር፣ ሽንት ቤት ግንባታ 10000/አስር ሺህ ብር እና የእጅ ፓምፕ ግንባታ 10000 አስር ሺህ ብር / በሁሉም ጨረታ CPO [...] ብቻ ማስገባት የሚችል/የምትችል። ለግንባታዎች ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ ፣ ለህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለውሃ ግንባታ WC ለሌሎች ግንባታ GCወይም BCሆኖ [...] ደረጃ አቅርበው የሚሆኑ [...]
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በፖስታ በማሸግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 የስራ ቀናት ፣በዋን ዋሽ ፕሮግራም ለሚሰራው ሽንት ቤት እና የእጅ ፓምፕ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ውስጥ በካፋ ዞን የሳይለም ወረዳ ፋ/ይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችል/የምትችል ሲሆን በዋን ዋሽ ፕሮግራም ለሚሰራው ሽንት ቤት እና የእጅ ፓምፕ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት
  10. ጨረታው በ21ኛው እና 10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
  11. ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ለተሸናፊው ወዲያውኑ ደረሰኙን ሲያቀርብ የሚመለስ ይሆናል።
  12. አሸናፊው ጨረታ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ውል ማስከበሪያ አስይዞ ውል የማይፈጽም ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  13. አሸናፊው ተወዳዳሪ ማሸነፉ ሲረጋገጥ ዕቃዎቹን በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ፋ/ይ/ኢ/[...] ቤት በጥራት ኮሚቴ ጥራቱ ሲረጋገጥ ንብረት ክፍል ማስረከብ የሚችል/የምትችል።

ማሳሰቢያ:- በዋን ዋሽ ፕሮግራም ለሚሰራው ሽንት ቤት እና የእጅ ፓምፕ ከወጣበት ቀን [...] ለ10 የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ይሆናል።

-መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መ[...] የተጠበቀ ነው። ጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ዕለት ሰንበት ወይም በ[...] በቀጣይ ሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

ለመረጃ መረጃ :- 0917091150/0912877747/0917753737/

Summary
Saylem Woreda Finance Office (Kafa Zone) invites bids for electronics, stationery, furniture, generator, lab machines, water items and repairs, and construction works incl. One WASH toilets and hand pumps.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender