Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0967441304
  • Website
  • Deadline15 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 1000 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 150,000 (CPO ወይም ከመድን ድርጅቶች ቦንድ)
  • opening dateበዛው እለት 8:30
  • Sector Building Construction

የጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት የጤና ኬላ MCH እና OPD ክፍል ግንባታ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/መ/ቁ/02/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት ለጤና ጽ/ቤት በ[...] ቀበሌ የ[...] ጤና ኬላ የአጠቃላይ ጤና ኬላ MCH & OPD ROOM በ2019 በጀት አመት በተያዘው ካፒታል በጀት ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን

  1. የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  2. የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ::
  3. ተቋራጭ በግንባታ ስራ ተቋራጭ በደረጃ BC-4/GC-5 እና ከዛ በላይ የሆኑና የዘመኑ ግብር የመክፈል ግዴታቸው የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው::
  4. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተቋራጮች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው::
  5. ተቋራጮች የብቃት ማረጋገጫ የ2019 የታደሰ የበጀት ዓመቱ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለባቸው::
  6. ተቋራጮች በግንባታ ስራ በአቅራቢነት በኦን ላየን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ ሰርተፊኬት e-GP /Electronic Government procurement/ ማቅረብ ይኖርባችኋል::
  7. የ2019 በጀት አመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance for 2019 EC)
  8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተቋራጮች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል::
  9. ተቋራጮች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ የተጠየቀውን መረጃ ብቻ በአግባቡ የሚያቀርቡ እና ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት ስርዝ ቢፈጠር በተፈጠረው ቦታ ፊርማ የማኖር ግዴታ መሆኑን መረዳት ይጠበቃል::
  10. ተቋራጮች የጨረታ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶከመት ሲያቀርቡ:-
    ሀ. ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት::
    ለ. ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ በድርጅቱ ባለስልጣን በእያንዳንዱ ገጽ የተፈረመበት እና ማህተም የተደረገበት ሆኖ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ (ፋይናንሻል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
  11. ተቋራጮች የግንባታ ስራው የሚሰራበት ቦታ በአካል በማየት ስለ ማየታቸው ከጌታ ወረዳ ከጤና ጽ/ቤት የተወከለ አካል የተፈረመበት እና ማህተም የተደረገበት መረጃ በመቀበል ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነዱ ጋር ማያያዝ ያስፈልጋል::
  12. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተቋራጮች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም::
  13. ተቋራጮች የጨረታ ማስከበሪያ 150,000/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO (በቼክ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለ148 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት::
  14. ግዥ ፈጻሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው የግንባታ ስራዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖረዋል::
  15. ተቋራጮች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታው ከመከፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሑፍ መሆን አለበት::
  16. በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተቋራጮች በግንባታ የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በተከታታይ እስከ 21ኛው ቀን 2:30 ድረስ የጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል::
  17. የጨረታ ሳጥኑ 21/ሃያ አንደኛ/ ቀን የሕዝብ-በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8:00 ሰአት በጨረታ ኮሚቴ ታሽጎ በዛው እለት 8:30 ተጫራቾች/ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል / ባይገኙም ይከፈታል::

ማሳሰቢያ

  1. ግዢ ፈጻሚው አካል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል::
  2. በአፈጻጸም ምክንያት በወረዳው/በዞን/በክልል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋራጮች መወዳደር አይችሉም
  3. ማንኛውም ተጫራች ለቴክኒካል ዶክመንት የተጠየቀውን መረጃ ብቻ ግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል::
  4. የቫት 7.5% የምንቀርጥ መሆኑን እናሳስባለን::
  5. ተጫራቾች ዋጋ ስትሞሉ ቫትን ባካተተ ሁኔታ መሙላት ይጠበቅባችኋል ካልሆነ ቫት እንደ ተካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል::

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0967441304/0973757244 መደወል ይችላሉ::

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽሕፈት ቤት

Summary
Geta Woreda Finance Office (Gurage Zone) invites BC-4/GC-5 and above contractors to build an MCH and OPD room at a health post for the woreda health office.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender

Development Bank of Ethiopia invites GC/BC Grade 7 and above contractors (Ref. DBE/NCB/W/05/2026/27)...

READ MORE
የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግቢ መግቢያ በርና አጥር ግንባታ ስራ

READ MORE