የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የግቢ መግቢያ በርና አጥር ግንባታ ስራ
Dalocha Poly Technic College (ዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
የአካባቢ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን ዳሎቻ ወረዳ ዳሎቻ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የግቢ መግቢያ በርና አጥር ሥራ በመስኩ የተሰማሩ መሐበራትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ደረጃቸው G.C/B.C-9 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፤
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤
- የጨረታ ዋስትና 80,000 (ሰማኒያ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤
- የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን ዳሎቻ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ካሉት 10 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ ዳሎቻ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 4:30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ:-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መከፈቻ ቀኑን አይለውጥም::
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 0925746727 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
በስልጤ ዞን የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Summary
Dalocha Polytechnic College (Silte Zone) invites GC/BC grade 9 and above contractors to bid for construction of its compound entrance gate and fence.
